Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ተጨማሪ መግለጫ 3—የሰብዓዊ ዘር ወንድማማችነት

    ክርስቶስ ለማንኛውም ልዩነት እውቅና አልሰጠም

    ክርስቶስ ለብሔረሰብ ወይም ለማዕረግ ወይም ለተወሰነ የእምነት አስተሳሰብ እውቅና አልሰጠም፡፡…ክርስቶስ የመጣው እያንዳንዱን የመለያ ግርግዳ ለማፍረስ ነበር፡፡ እርሱ የመጣው የእርሱ የምህረት እና የፍቅር ሥጦታ እንደ አየር፣ እንደ ብርሐን ወይም ምድርን እንደሚያረሰርሰው ዝናብ ያልተገደበ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ Amh2SM 485.1

    የክርስቶስ ሕይወት የመሰረተው ኃይማኖት የዘር ልዩነት የሌለበት፣ አይሁድና አህዛብ፣ ጨዋና ባሪያ በጋራ ወንድማማችነት የተገናኙበትና በእግዚአብሔር ፊት እኩል የሆኑበት ኃይማኖት ነው፡፡ ማንኛውም የፖሊሲ ጥያቄ በእርሱ እንቅስቃሴዎች ላይ ተጽእኖ አላሳደረም፡፡ በጎረቤቶችና በእንግዶች፣ በወዳጆችና በጠላቶች መካከል ምንም ልዩነት አላደረግም፡፡ ለእርሱ ልብ አስደሳች የነበረው የሕይወት ውኃን ይጠማ የነበረ ነፍስ ነበር፡፡. . . .Amh2SM 485.2

    ክርስቶስ እጅግ ሸካራ የሆኑና ብዙ እምነት የማይጣልባቸው ሰዎች እንደ እግዚአብሔር ልጆች እንዲታዩ የሚያደርጋቸውን ባሕርይ በማግኘት ነቁጣና ጉዳት የለሽ መሆን እንዲችሉ በማድረግ በተስፋ ለመምራት ፈለገ፡፡ --The Ministry of Healing, pp. 25, 26Amh2SM 485.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents