Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ኤለን ኋይት ምንም ዓይነት ተአምራቶች አልፈጸመችም

    አንዳንዶች «ሚስስ ኢ. ጂ. ኋይት ምንም ተአምራት አትሰራም” በማለት ጌታ እንድሰራ በሰጠኝ ሥራ ላይ አለማመናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ተአምራቶችን እንደ መለኮታዊ ምሪት ምልክት አድርገው የሚመለከቱ ሰዎች አሰቃቂ በሆነ የመታለል አደጋ ውስጥ ናቸው፡፡ ጠላት ከእምነት በተለዩ ወኪሎቹ አማካይነት እንደሚሰራና እነርሱ በሰዎች ፊት ከሰማይ እሳት እስከማውረድ ድረስ የሚመስሉ ተአምራቶችን እንደሚሰራ በቃሉ ውስጥ ተገልጾአል፡፡ ሰይጣን፣ «በውሸት ድንቆች» አማካይነት፣ ከተቻለው የተመረጡትን እንኳን ያስታል፡፡ {2SM 53.4}Amh2SM 53.4

    ብዙ ሰዎች ስናገር አድምጠውኛል፣ ጽሁፎቼንም አንብበዋል፣ ነገር ግን ተአምራት ሰርቻለሁ ስል አንድም ሰው አዳምጦኝ አያውቅም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለታመሙ ሰዎች እንድጸልይ ተጠርቻለሁ፣ የእግዚአብሔር ቃልም ተረጋግጧል፡፡ [ያዕቆብ 5፡ 14፣ 15 ተጠቅሷል፡፡] ክርስቶስ ታላቅ ተአምራት ሰሪ ነው፡፡ ለእርሱ ክብር ሁሉ ይሁን፡፡ --Letter 410, 1907. {2SM 54.1}Amh2SM 54.1