Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 18—ለዲ ኤም ካንራይት የቀረበ ተማጽኖ

    [Appeared In Notebook Leaflets, The Church, No. 8.]

    ባትል ክሪክ

    ኦክቶበር 15፣ 1880

    ኤልደር ዲ ኤም ካንራይት,

    (ከዲ. ኤም. ካንራይት ጋር የተደረጉ ሌሎች ግንኙነቶች ቀጥሎ ባለው ጽሁፍ ውስጥ ይገኛሉ)፡

    ቴስቲሞኒስ 3ኛው መጽሐፍ ገጽ 304-329፣ ኦገስት 12 ቀን 1873 ዓ.ም ለወጣት አገልጋይና ለባለቤቱ፤ 5ኛው መጽሐፍ ገጽ 516-520፣ በ1886 አከባቢ፣ ለሕጻናት ምቹ የሆነ ንባብ፤ 5ኛው መጽሐፍ ገጽ 571-573፣ 1887 ዓ.ም አስገራሚ ሕልም፤ 5ኛው መጽሐፍ ገጽ 621-628፣ ሚያዚያ 20፣ 1887 ዓ.ም፣ ደብዳቤ በሚሉ ርዕሶች ስር ይገኛሉ፡፡ Amh2SM 162.1

    ውድ ወንድም፡-

    ውሳኔህን በመስማቴ አዝኛለሁ፣ ነገር ግን እንደዚህ እንደምትወስን የምጠብቅበት ምክንያት ነበረኝ፡፡ አሁን እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚፈትንበትና ብቃታቸውን የሚያረጋግጥበት ጊዜ ነው፡፡ የሚበጠር ነገር ሁሉ ይበጠራል፡፡ ነፍሶቻቸው ከዘላለማዊው ዓለት ጋር የተጣበቀ ብቻ ይቆማሉ፡፡ በራሳቸው ማስተዋል የሚደገፉ፣ ያለማቋረጥ በክርስቶስ የማይኖሩ፣ እንደዚህ ዓይነት ለውጥ ይደርስባቸዋል፡፡ እምነትህ በሰው ላይ ተመስርቶ ከሆነ እነዚህን የመሳሰሉ ለውጦች እንጠብቃለን፡፡ {2SM 162.1}Amh2SM 162.2

    እንደ ሕዝብ ከእኛ ጋር ያለህን ግንኙነት ለማቋረጥ ወስነህ ከሆነ ለራስህና ለክርስቶስ ብዬ አንድ የምጠይቅህ ጥያቄ አለኝ፡- ከሕዝባችን ራቅ፣ እየጎበኘሃቸው ጥርጣሬህንና ጨለማህን በመካከላቸው አትናገር፡፡ ከኢየሱስ ባንዲራ ሥር ወጥተህ በሰይጣን ባንድራ ሥር ስለሆንክ እርሱ በሚያስፈነድቅ ደስታ ተሞልቷል፡፡ በአንተ ውስጥ መንግሥቱን ለመገንባት ጠቃሚ ወኪል አድርጎ መጠቀም የሚችልበትን ነገር ያያል፡፡ ለፈተና ከተሸነፍክ እንደምትከተል ስጠብቀው የነበረውን ያንኑ መንገድ እየተከተልክ ነህ፡፡ {2SM 162.2}Amh2SM 162.3

    ሁልጊዜ የሥልጣንና ታዋቂ የመሆን ፍላጎት ነበረህ፣ አሁን ላለህበት ቦታ እንድትበቃ ካደረጉህ ምክንያቶች አንዱ ይህ ነው፡፡ ነገር ግን ጥርጣሬዎችህንና ጥያቄዎችህን ለራስህ አድርጋቸው፡፡ ሰዎች አንተ ካለህ በላይ የዓላማ ብርታትና የባሕርይ ጽናት እንዳለህ አድርገው ዋጋ ሰጥተውሃል፡፡ ጠንካራ ሰው እንደሆንክ አስበዋል፤ ጨለማ የሆኑ ሀሳቦችህንና ስሜቶችን ስትተነፍስ እነዚህን ሀሳቦችና ስሜቶች በማታለል ኃይላቸው እጅግ ኃይለኛ ለማድረግ ሰይጣን ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃል፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን በመረጠና በድፍረት ራሱን በሰይጣን ወገን፣ በጠላት ጎራ ባሰለፈ በአንድ ነፍስ ተጽእኖ ብዙ ነፍሳት ተታለው ይጠፋሉ፡፡ {2SM 163.1}Amh2SM 163.1

    ከመጠን በላይ ለመሆንና በዓለም ላይ ጉረኛና ብዙ ድምጽ የምታሰማ ለመሆን ፈልገሃል፣ ከዚህ የተነሳ በእርግጠኝነት ፀሐይህ በጨለማ ውስጥ ትጠልቃለች፡፡ በየቀኑ ዘላለማዊ ክስረትን እየተጋፈጥህ ነህ፡፡ በትምህርቱ ቸልተኛ የሆነ ልጅ ወላጁንና መምህሩን እያታለለ እንደሆነ ያስባል፤ ነገር ከፍተኛ የሆነ ክስረት እየደረሰበት ያለው ማን ነው? እራሱ አይደለምን? ራሱን እያታለለ እና ሊኖረው የሚችለውን እውቀት ከራሱ እየነጠቀ አይደለምን? መልካም ሥራን በመስራት፣ የክርስቶስን ምሳሌ በመቅዳት ብቁ እንድንሆን እግዚአብሔር ይፈልጋል፤ ነገር ግን የቸልተኝነትን ሚና እየተጫወትክ ነህ፣ ነፍስህን ለጥፋት እስከመዳረግ ድረስ የሚነድፍና የሚመርዝ ስሜት እየተንከባከብክ ነህ፣ አስፈላጊ በሆኑ ዘላለማዊ ነገሮች ላይ ቸልተኛ እየሆንክ ነህ፣ ነፍስህን ከክርስቶስ የእውቀት ሙላትና ብልጽግና እየቀማህ ነህ፡፡ ፍላጎትህ እጅግ ወደ ላይ ከመነሳቱ የተነሳ ራስን ከፍ ከፍ ከማድረግ ያነሰ ምንም ነገር አይቀበልም፡፡ ራስህን አታውቅም፡፡ ሁልጊዜ ያስፈልግህ የነበረው ትሁትና የሚጸጸት ልብ ነበር፡፡ {2SM 163.2}Amh2SM 163.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents