የችኮላ ውሳኔዎች
የአንድን ሰው ሁኔታ ለዘላለም የሚወስኑ ውሳኔዎች በቅጽበት ሊፈጸሙ ይችላሉ፡፡ ሰይጣን ወደ ክርስቶስ በመጣበት ሁኔታ ዓለማዊ ክብርንና ግርማን በማቅረብ ወደ አንተ መጥቷል፡፡ ፈቃደኛ ከሆንክ ለእርሱ የበላይነት እውቅና ትሰጣለህ፡፡ አሁን እያደረግክ ያለኸው ይህንን ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ተጨማሪ እርምጃ ከመውሰድህ በፊት እንድታስብበት እማጸንሃለሁ፡፡ {2SM 165.1}Amh2SM 165.1
አንተን በተመለከተ መላእክት ምን እየመዘገቡ ናቸው? ያንን መዝገብ የምትጋፈጠው እንዴት ነው? ድንገተኛ ለሆነው ክህደት ለእግዚአብሔር ምን ምክንያት ታቀርባለህ? ትልቅ ሥራ የመስራት ፍላጎት ሁል ጊዜ አብሮህ ነበር፡፡ ትንሹን ሥራህን አስበህበትና በታማኝነት በማድረግ ረክተህ ቢሆን ኖሮ በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያገኝ ነበር፡፡ ነገር ግን አስታውስ፣ ለትንሽ ጊዜ በፈተና መሸነፍና ያለማሰብ የሚያበላሸውን ነገር ለመመለስ የሕይወት ዘመን ሥራን ሊጠይቅ ይችላል፡፡ {2SM 165.2}Amh2SM 165.2
ወደ ተሻለ አገር እየተጓዝን ያለን እንግዶችና መጻተኞች ነን፤ ነገር ግን ለአንተና ለእኔ ከሰማይ ዜጎች ጋር የሚስማማ ልብ ሳይኖረን በሰማይ ከመሆን ይልቅ በእርሻ ውስጥ ለማረስ የጋማ ከብት ብንሆን ይሻላል፡፡ ፈቃድህን ለጥቂት ጊዜ በመፈጸም ራስህን በሰይጣን ኃይል ሥር ታስቀምጣለህ፣ ነገር ግን የእርሱን የእግር ብረት ለመስበርና ከፍ ወዳለው ቅዱስ ሕይወት ለመድረስ ለትንሽ ጊዜ ፈቃድህን ከመፈጸም የበለጠ ነገር ይሻል፡፡ ዓላማው ተመስርቶ፣ ሥራው ተጀምሮ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ተፈጻሚነቱ ልፋትን፣ ጊዜን፣ አለመሰልቸትን፣ ትዕግሥትንና መስዋዕትነትን ይጠይቃል፡፡ ሆን ብሎ በሙሉ ብርሃን ከእግዚአብሔር የሚለይ ሰው ለመመለስ ፊቱን ማዞር ሲፈልግ በመንገዱ ላይ እሾክና አሜካለ በቅሎ ያገኛል፤ ይህ ሰው ቆስለው በሚደሙ እግሮች ረዥም መንገድ ለመጓዝ ቢገደድ መደነቅ ወይም ተስፋ መቁረጥ የለበትም፡፡ እጅግ አስፈሪውና ሰው ከተሻለ ሁኔታ መውደቁን የሚያሳይ እጅግ መፈራት ያለበት ማስረጃ ለመመለስ የሚጠይቀው ዋጋ እጅግ ብዙ መሆኑ ነው፡፡ የመመለሻው መንገድ ሊገኝ የሚችለው ስንዝር በስንዝር፣ በየሰዓቱ ጠንክሮ በመዋጋት ብቻ ነው፡፡ {2SM 165.3}Amh2SM 165.3
የሰማይ መንገድ ማዕረግና ሀብት እንዳይሄዱበት እጅግ ጠባብ ነው፣ ለምኞት ጨዋታም እጅግ ጠባብ ነው፣ የምቾት ሰረገላዎች እንዳይወጡበት እጅግ ቀጥ ያለ ዳገት ያለበትና ወጣ ገባ ነው፡፡ ልፋት፣ ለክርስቶስ ትዕግሥት፣ ራስን መስዋዕት ማድረግ፣ መነቀፍ፣ ድህነት፣ ከባድ ሥራ፣ ይደርስበት የነበረውን የኃጢአተኞችን ተቃውሞ መታገስ ድርሻው ስለነበር ሰውም ወደ እግዚአብሔር ገነት የሚገባ ከሆነ ይህ ድርሻው መሆን አለበት፡፡ {2SM 166.1}Amh2SM 166.1
የአሁኑን እምነትህን በቀላሉ ትተህ ከሆነ ይህ የሆነበት ምክንያት ዋና ሥርን አጥብቆ በሚይዝ እምነት ውስጥ ወደ ታች ሥር ስላልሰደድክ ነው፡፡ የከፈልከው ዋጋ እጅግ ትንሽ ነው፡፡ በፈተና ካላቆመህና በመከራ ካላጽናናህ ምክንያቱ እምነትህ በጥረት ስላልጠነከረና በመስዋዕትነት ስላልነጻ ነው፡፡ ለክርስቶስ መከራ ለመቀበል ፈቃደኛ የሆኑት ክርስቶስ እንደወደዳቸው በማሳየት እርሱ ለእነርሱ መከራ ከተቀበለው ይልቅ እነርሱ በመሰቃየታቸው የበለጠ ደስታ ያገኛሉ፡፡ ሰማይን የሚያገኙ ሰዎች የልፋታቸውን ፍሬ ለማጨድ የከበሩ ጥረቶችን ያደርጋሉ፣ በብዙ ትዕግሥትም ይሰራሉ፡፡ {2SM 166.2}Amh2SM 166.2
ፈተናን ተቋቁመው ላለፉት እና ለክርስቶስ ፍቅር ብለው ዓለምን፣ የዓለምን ክብርና ሙገሳ በመተው ክርስቶስን በሰዎች ፊት ላመኑት እና እርሱ በአባቱና በመላእክት ፊት እስኪያምናቸው ድረስ በትዕግሥት ለጠበቁት የገነትን ደጆች በሰፊው የሚከፍት እጅ አለ፡፡ {2SM 166.3}Amh2SM 166.3