Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    መድሃኒቶችን በመደገፍ መመስከር አልችልም

    መድሃኒት መስጠት የሚያስከትለውን ብዙ ጉዳት ካየሁ ወዲህ አልጠቀማቸውም፣ ስለ ጠቃሚነታቸውም ምስክርነት አልሰጥም፡፡ ጌታ ለሰጠኝ ብርሃን እውነተኛ መሆን አለብኝ፡፡Amh2SM 293.3

    የጤና ተቋማችን መጀመሪያ በተመሰረተበት ጊዜ እንሰጥ የነበረው ሕክምና በሽታን ለመቋቋም ልባዊ ጥረትን ጠይቋል፡፡ የተዘጋጁ መድሃኒቶችን አልተጠቀምንም፤ የተከተልነው የንጽህና አጠባበቅ ዘዴዎችን ነበር፡፡ ሕይወትን ለማዳን ሰብዓዊ መሣሪያዎች ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር የሚችሉበት ሥራ ነበር፡፡ ክፉ ተጽእኖውን ጥሎ የሚያልፍ ምንም ነገር ቢሆን በሰብአዊ አካል ውስጥ መጨመር የለበትም፡፡ የጤና ማሰልጠኛ ተቋማትን በተለያዩ ቦታዎች ማቋቋም ስለማስፈለጉ የተሰጠው ምክንያት በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰጠውን ብርሃን ለመተግበር፣ የንጽህና አጠባበቅ ሕክምናን ለመለማመድ እና በሽተኛን ማከም የሚቻልባቸውን የተለያዩ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ለማስተማር ነበር፡፡Amh2SM 293.4

    ብዙ ተማሪዎች ስለ መድሃኒቶች አጠቃቀም ትምህርት ለማግኘት ወደ---- እንዲሄዱ በመደፋፈራቸው ሀዘን ተሰምቶኝ ነበር፡፡ እኔ የተሰጠኝ ብርሃን በ---- ወይም በጤና ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ መድሃኒቶች ጥቅም ላይ ከሚውሉበት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የተለየ መልክ አለው፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ እውቀት ማግኘት አለብን፡፡ ለመድሃኒቶች የተሰጡ ውስብስብ ስሞች ሰዎች በመዝገበ ቃላት ውስጥ ፈልገው ትርጉማቸውን ካላወቁ በስተቀር እንደ መድሃኒትነት የተሰጣቸው ነገር ምን እንደሆነ እንዳያውቁ ጉዳዩን ለመደበቅ የተሰጡ ናቸው፡፡Amh2SM 293.5

    አንዳንድ ጊዜ ጠቃሚ የሆኑና በመስክ የሚያድጉ ቀላል እጽዋትን እግዚአብሔር ሰጥቷል፤ እነዚህን እጽዋት በሕመም ጊዜ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል እያንዳንዱ ቤተሰብ ቢማር ኖሮ ብዙ ስቃይን መከላከል ይቻል ነበር፣ ሐኪምን መጥራትም አያስፈልግም ነበር፡፡ እነዚህ ጊዜ ያለፈባቸው ቀላል እጽዋት በብልህነት ጥቅም ላይ ቢውሉ ኖሮ የመድሃኒት ሕክምናን እየወሰዱ የሞቱትን ብዙ ሕመምተኞች በፈወሱ ነበር፡፡Amh2SM 294.1

    እጅግ ጠቃሚ ከሆኑ ፈውሶች መካከል አንዱ በከረጢት ተደርጎ ለመታጠን ጥቅም ላይ የሚውለው የደቀቀ ከሰል ነው፡፡ ይህ እጅግ የተዋጣለት መፈወሻ ነው፡፡ ረጥቦ ስማርትዊድ ከሚባል ተክል ጋር ቢፈላ የተሻለ ነው፡፡ ሕመምተኞች ከፍተኛ የሆነ ሥቃይ እየደረሰባቸው እና ሐኪም የሕይወታቸው መጨረሻ ሊሆን ነው ብሎ ማሰቡን እንደ ምስጢር በነገረኝ ሰዓት ያዘዝኩት ይህን ነበር፡፡ ያኔ ከሰል እንዲሰጠው አስተያየት ሰጠሁ፤ ሕመምተኛው አንቀላፋ፣ ለውጥ መጣና ሕመምተኛው ከሕመሙ አገገመ፡፡ የተቀጠቀጠ እጅና እብጠት ላለባቸው የቆሰሉ ተማሪዎች ይህን ቀላል ፈውስ አዝዤላቸው ውጤቱ ፍጹም የተሳካ ነበር፡፡ የእብጠት መርዝ ተሸንፎ፣ ሕመም ተወግዶ ፈጣን ፈውስ ተፈጸመ፡፡ እጅግ ከባድ የሆነ የዓይን መመረዝ በከረጢት ተደርጎ እንደ አመቺነቱ በፈላ ወይም በቀዝቃዛ ውኃ ውስጥ የተነከረ ከሰልን በመያዝ ሊሻል ይችላል፡፡ ይህ እንደ አስማት ይሰራል፡፡Amh2SM 294.2

    በዚህ ሀሳብ እንደምትስቁ እጠብቃለሁ፤ ነገር ግን ለዚህ ቀላል ፈውስ ከእኔ በቀር ማንም የማያውቀውን የውጭ ሀገር ስም ብሰጠው ኖሮ የበለጠ ተጽእኖ ይኖረው ነበር፡፡ ነገር ግን እጅግ ቀላል የሆኑ ፈዋሽ ነገሮች ተፈጥሮን ሊያግዙ ይችላሉ፣ ከተጠቀምንባቸው በኋላም ምንም ዓይነት ክፉ ውጤት አስከትለው አያልፉም፡፡ Letter 82, 1897 (To Dr. J. H. Kellogg).Amh2SM 294.3