Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 41—በአንዳንድ የጋብቻ ሁኔታዎች ላይ የተሰጡ ምክሮች

    ሁለተኛ ጋብቻ ትክክለኛነት የተረጋገጠበት አጋጣሚ

    ሴት ልጅህ ጄ ከሚባል ሰው ጋር የፈጸመችውን ጋብቻ በተመለከተ እምን ላይ እንደተቸገርክበት አያለሁ፡፡ ነገር ግን ጋብቻው የተፈጸመው ከእናንተ አዎንታን በማግኘት ሲሆን ሴት ልጃችሁም ስለ እርሱ ሁሉንም ነገር እያወቀች እንደ ባለቤቷ አድርጋ የተቀበለችው እስከሆነ ድረስ አሁን በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ሸክም የምትሸከሙበትን ምክንያት አላይም፡፡ ልጃችሁ ልጄን ስለምትወደው ሁለቱም ጥሩ የሆነ የክርስቲያን ልምምድ እንዲኖራቸውና ጉድለት ባለባቸው ቦታ ላይ እንዲገነቡ ይህ ጋብቻ በእግዚአብሔር የተፈቀደ ሊሆን ይችላል፡፡ ልጃችሁ ከልጄ ጋር የጋብቻ ቃል ኪዳን ስለፈጸመች የፈጸመችውን ቃል ኪዳን ማፍረስ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ እርሷ ያለባትን ግዴታዎች መሰረዝ አትችልም፡፡….ኬ ከምትባል የመጀመሪያ ሚስቱ ጋር የነበረውን ግንኙነት አውቃለሁ፡፡ ጄ ኬን ከልክ በላይ ይወዳት ነበር፤ እርሷ ግን የእርሱ ፍቅር የሚገባት አልነበረችም፡፡ እሷን ለመርዳት አቅሙ የሚፈቅደውን ሁሉ አድርጓል፣ በሚቻለው ሁሉ ሚስቱ አድርጎ ሊያቆያትም ፈልጎ ነበር፡፡ ካደረገው የበለጠ ማድረግ የሚችለው ነገር አልነበረውም፡፡ ፍቺ እንዳትፈጽም ተማጸንኳት፣ እየተከተለች ያለችው መንገድ ትክክል አለመሆኑን ለማሳየት ሞከርኩ ለመንኳትም፤ ነገር ግን እሷ በአቋሟ የጸናች፣ የማታወላውል፣ ትዕቢተኛ እና የራሷን መንገድ መከተል የምትፈልግ ነበረች፡፡ ከእርሱ ጋር አብራ በኖረችበት ጊዜ ከእርሱ ማግኘት የምትፈልገውን ገንዘብ ሁሉ ለማግኘት ፈለገች፣ ነገር ግን ሚስት ባሏን መያዝ እንደሚገባት አትይዘውም ነበር፡፡Amh2SM 339.1

    ጄ ሚስቱን አላባረራትም፡፡ እሷ ትታው በመሄድ ሌላ ወንድ አገባች፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እሱ እንዳያገባ የሚከለክል ምንም ነገር አላይም፡፡ የሴት ፍቅርን የማግኘት መብት አለው፡፡Amh2SM 340.1

    ይህ አዲስ አንድነት የሚረበሽበትን ምክንያት አላይም፡፡ አንድን ሰው ከሚስቱ መለየት ከባድ ነገር ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እንደዚህ ዓይነት እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለም፡፡ እሱ አልተዋትም፣ የተወችው እሷ ነች፡፡ እሷ ሰማኒያዋን እስክትቀድ ድረስ እርሱ እንደገና አላገባም፡፡ ኬ በፈታችው ጊዜ ጄ እጅግ ተሰቃይቷል፣ ኬ ሌላ ሰው እስክታገባ ድረስ ጄ ሌላ ሚስት አላገባም ነበር፡፡ አሁን የመረጣት ሴት እንደምትረዳውና እሱም ሊረዳት እንደሚችል እርግጠኝነት ይሰማኛል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ከእሱ እንድትለይ የሚጠይቅ ምንም ነገር አላይም፡፡ ምክሬን ስለጠየቃችሁ በነጻ እሰጣችኋለሁ፡፡ Letter 50, 1895.Amh2SM 340.2