Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 25—በመከራ ውስጥ ጽናት

    ይህ መከራ ለምን?

    (በ1891 ዓ.ም መገባደጃ ላይ ኤለን ኋይት ከጄኔራል ኮንፈራንስ በቀረበላት ጥያቄ መሠረት አዲስ የተመሰረተውን ሥራ በማጠናከር ሂደት ውስጥ ለማገዝ ወደ አውስትራሊያ ተጓዘች፡፡ እዚያ የነበረው ቆይታ ለዘጠኝ ወራት ተራዘመ፡፡ እዚያ እንደደረሰች ወዲያውኑ የተራዘመና ሥቃይ ያለበት ሕመም ያዛት፡፡ ቀጥለው ያሉት ነገሮች በነበረባት ሥቃይ ውስጥ የነበራት ጽናት ዝርዝር ናቸው፡፡ ከዚህ ልምምድ የተማረቻቸውን ትምህርቶች ልብ በሉ፡፡ አሰባሳቢዎች)፡፡Amh2SM 233.1

    እያንዳንዱ የፖስታ አድራሻ ከእጄ ከአንድ መቶ እስከ ሁለት መቶ ገፆችን ተቀብሏል፤ ከዚህ ውስጥ አብዛኛው የተጻፈው አሁን በአልጋ ላይ በትራስ ተደግፌ ባለሁበት ሁኔታ በግማሽ ተኝቼ ወይም በግማሽ ተቀምጬ፣ ወይም በማይመች ወንበር ላይ በድጋፍ ተቀምጬ ነው፡፡ Amh2SM 233.2

    ስቀመጥ በዳሌዬና በታችኛው አከርካሪዬ ላይ በጣም ያመኝ ነበር፡፡ በዚህ አገር ውስጥ (አውስትራሊያ) በጤና ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ ያሉአችሁ ዓይነት ቀላል ወንበሮች የሚገኙ ቢሆኑና አንዱ በሰላሳ ዶላር የሚገኝ ቢሆን ኖሮ እኔ አንዱን እገዛ ነበር፡፡ ቀጥ ብዬ የምቀመጠውና ራሴን ቀና የማደርገው በትልቅ ድካም ነው፡፡ በወንበሩ በስተኋላ በኩል በትራስ ላይ ግማሽ አጋድዬ ማሳረፍ አለብኝ፡፡ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ይህ ነው፡፡Amh2SM 233.3

    ነገር ግን ተስፋ አልቆረጥኩም፡፡ በየቀኑ የሚያስፈልገኝ ነገር እየተሰጠኝ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ሌሊቱን እንቅልፍ ከጥያቄ ውጭ በሆነባቸው ረዥም አድካሚ ሰዓቶች ውስጥ ብዙ ሰዓት ለጸሎት ሰጥቻለሁ፤ እያንዳንዱ ነርቭ ከሕመም የተነሣ የተጨራመተ በመሰለ ጊዜ፣ የራሴን ሁኔታ ከግምት ውስጥ አስገብቼ ተስፋ የምቆርጥ በመሰለኝ ሰዓት በምሥጋና እንድሞላ በሚያደርገኝ መጠን የክርስቶስ ሰላም በልቤ ውስጥ መጥቶ ነበር፡፡ ኢየሱስ እንደሚወደኝ አውቃለሁ፣ እኔም እወደዋለሁ፡፡ ሌሊት እተኛ የነበረው አንዳንድ ጊዜ ሶስት ሰዓት፣ ጥቂት ሌሊቶች ደግሞ አራት ሰዓት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ እተኛ የነበረው ሁለት ሰዓት ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም በእነዚህ ረዥም የአውስትራሊያ ሌሊቶች በጨለማ ውስጥ ዙሪያው ሁሉ የበራ ይመስል ስለነበር ከእግዚአብሔር ጋር ጣፋጭ ግንኙነት በማድረግ እደሰት ነበር፡፡Amh2SM 233.4

    መጀመሪያ ተስፋ አስቆራጭ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ራሴን ባገኘሁ ጊዜ ሰፊ ውኃዎችን አቋርጬ በመምጣቴ በጥልቀት ተጸጽቼ ነበር፡፡ ለምን በአሜሪካ አልሆንኩም? ይህን ሁሉ ዋጋ ከፍዬ እዚህ አገር የሆንኩት ለምንድን ነው? በተደጋጋሚ ፊቴን በአልጋ ልብስ ውስጥ በመቅበር በደንብ አልቅሻለሁ፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ በእንባ ምቾት አላሳለፍኩም፡፡Amh2SM 234.1

    ለራሴ እንዲህ አልኩ፣ «ኤለን ጂ ኋይት፣ ምን ማለትሽ ነው? ወደ አውስትራሊያ የመጣሽው ኮንፍራንሱ ለአንቺ የተሻለ ነው ወዳለበት ቦታ መሄድ ሃለፊነትሽ እንደሆነ ስለተሰማሽ አይደለምን? ይህ ልምምድሽ አልነበረምን?”Amh2SM 234.2

    ለራሴ መልሼ «አዎን» አልኩ፡፡ Amh2SM 234.3

    እንደገና «ታዲያ እንደተተውሽ የሚሰማሽ እና ተስፋ የምትቆርጭው ለምንድን ነው ? ይህ የጠላት ሥራ አይደለምን?” ብዬ ራሴን ጠየቅኩ፡፡Amh2SM 234.4

    ለራሴ መልሼ «የጠላት ሥራ እንደሆነ አምናለሁ” አልኩ፡፡Amh2SM 234.5

    በተቻለ ፍጥነት እምባዬን ጠራረግኩና እንዲህ አልኩ፣ «ይበቃል፤ ከዚህ በኋላ ጨለማ ያለበትን በኩል አላይም፡፡ ብኖርም ብሞትም የነፍሴን ጥበቃ ለእርሱ ለሞተልኝ አሳልፌ እሰጣለሁ፡፡»Amh2SM 234.6

    ከዚያ በኋላ ጌታ ሁሉንም ነገር ለበጎ እንደሚያደርግ ስላመንኩ በእነዚህ ረዳተ-ቢስ በነበርኩባቸው ስምንት ወራት ውስጥ ምንም ዓይነት ሀዘንም ሆነ ጥርጣሬ አልነበረኝም፡፡ አሁን ይህን ጉዳይ የማየው በዚህ አገር ስላለው ሕዝቡ፣ በአሜሪካ ላሉት እና ለእኔም ጥቅም እግዚአብሔር ያለው ታላቅ እቅድ አካል አድርጌ ነው፡፡ ለምንና እንዴት እንደሆነ ማስረዳት አልችልም፣ ነገር ግን አምነዋለሁ፡፡ በመከራዬም ደስተኛ ነኝ፡፡ ሰማያዊ አባቴን መታመን እችላለሁ፡፡ ፍቅሩን አልጠራጠርም፡፡ ሁልጊዜ ቀንና ማታ ነቅቶ የሚጠብቀኝ ጠባቂ አለኝ፣ በአመስጋኝነት ከተሞላ ልብ ስለሚመጣ ምስጋናው በከናፍሮቼ ላይ ነውና ጌታን አወድሳለሁ፡፡ Letter 18a, 1892.Amh2SM 234.7

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents