Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አስተምህሮን የመረዳት አስፈላጊነት

    አመጽና ክህደት በምንተነፍሰው አየር ውስጥ ናቸው፡፡ ረዳተ-ቢስ ነፍሶቻችንን በእምነት በክርስቶስ ላይ ካላቆየን በስተቀር በዚህ ተጠቂዎች እንሆናለን፡፡ ሰዎች እንዲህ በቀላሉ ወደ ስህተት የሚመሩ ከሆነ ሰይጣን ክርስቶስን መስሎ ተአምራቶችን ሲሰራ እንዴት መቆም ይችላሉ? ሰይጣን በአካል ክርስቶስን በመምሰልና ክርስቶስ ነኝ እያለ ክርስቶስ የሚሰራቸውን ሥራዎች በግልጽ እየሰራ ሲመጣ የማይናወጥ ማን ነው? የእግዚአብሔር ሕዝብ ለሀሰተኛው ክርስቶስ እንዳይታዘዙ ምን ይከለክላቸዋል? «…እነርሱን ተከትላችሁ አትሂዱ፡፡» {2SM 58.1}Amh2SM 58.1

    አስተምህሮዎች በግልጽ ሊስተዋሉ ይገባል፡፡ እውነትን ለማስተማር ተቀባይነት ያገኙ ሰዎች መልህቃቸውን ወደ ባሕር መጣል አለባቸው፤ ከዚያ በኋላ መልህቁ አጽንቶ ስለሚይዛቸው መርከባቸው ሞገዱንና ወጀቡን መቋቋም ይችላል፡፡ ማታለያዎች እየጨመሩ ይሄዳሉ፡፡ -- Letter 1, 1897. {2SM 58.2}Amh2SM 58.2

    ሰይጣን ነፍሳትን ለማሳት ከዚህ በፊት ከነበረው ይልቅ ተግቶ የሕይወት ጨዋታን በመጫወት ላይ ስለሚገኝ ሁሉ ጊዜ በመጠበቂያችን ላይ ካልሆንን በስተቀር በልባችን ውስጥ ኩራትን፣ የራስ ፍቅርን፣ የዓለም ፍቅርንና ብዙ ሌሎች ክፉ ባሕርያትን ይመሰርታል፡፡ በእግዚአብሔር እና በቃሉ እውነቶች ላይ ያለን እምነታችን እንዳይጸና ለማናጋት ሊያገኝ የሚችለውን እያንዳንዱን መሳሪያ ይጠቀማል፡፡ በእግዚአብሔር ነገሮች ላይ ጥልቅ ልምምድ ከሌለን፣ የተሟላ የቃሉ እውቀት ከሌለን፣ በጠላት ስህተቶችና ለማሳሳት በታቀዱ የሀሰት መከራከሪያዎች ለጥፋት እንታለላለን፡፡ እውነትን ከስህተት ለመለየት ስላልተማሩ የሀሰት አስተምህሮዎች የብዙዎችን መሰረቶች ይሸረሽራሉ፡፡ ከሰይጣን ማታለያዎች የምናመልጥበት ብቸኛው መከላከያችን ቅዱሳን መጻሕፍትን ተግቶ ማጥናት፣ ስለ እምነታችን ላሉን ምክንያቶች ብልህነት ያለበት መረዳት እና እያንዳንዱን የሚታወቅ ተግባር በታማኝነት መፈጸም ነው፡፡ አንድን የሚታወቅ ኃጢአት መፈጸም ድክመትንና ጨለማን በማስከተል ኃይለኛ ለሆነ ፈተና ያጋልጠናል፡፡ --The Review and Herald, Nov. 19, 1908. {2SM 58.3}Amh2SM 58.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents