Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ውሸት የእውነትን ቅርጽ ይይዛል

    እያንዳንዱ ሊታሰብ የሚችል መልእክት የእግዚአብሔርን ሥራ ለማስመሰል እየመጣ ነው፣ ሲመጣም ሁል ጊዜ በባንዲራው ላይ የእውነትን ቅርጽ ይዞ ነው፡፡... {2SM 92.3}Amh2SM 92.3

    በተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድ ቦታ ውስን የሆነ የሰብዓዊ ፍጡርን አስተሳሰቦችና መከራከሪያዎች፣ ሕልሞች፣ ምልክቶች እና ቅርጾች መተካት ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ተግባሮቻችን፣ ቃላቶቻችን፣ መንፈሳችን እና ተጽእኖዎቻችን ይታያሉ ይተቻሉም፡፡ እግዚአብሔር አገልጋዮቹ እንዲሆኑ የመረጣቸው ሰዎች በቃሉ ጸንተው ማረፍና የእግዚአብሔር ቃል የመጨረሻውን ውሳኔ ሰጭ እንዲሆን መፍቀድ አለባቸው፡፡ ... {2SM 93.1}Amh2SM 93.1

    የችኮላ ውሳኔ፣ ያለ በቂ ማስረጃ በግድ የለሽነት የተፈጠሩ አስተሳሰቦች፣ ከሌሎች ጊዜያቶች ሁሉ ይልቅ በአሁኑ ጊዜ እጅግ አጥፊ የሆኑ ውጤቶችን ያስከትላሉ፡፡ መንስኤንና ውጤትን የሚያሳዩ ምልክቶችን ስንመለከት አንዳንድ በፍጹም ሊስተካከል የማይችል ጉዳት ተከስቶ እናገኛለን፡፡ ለእግዚአብሔር መንጋ በደንብ የተበጠረ ንጹህ ምግብ ለመመገብ እንዴት ያለ ጥበብ እና የታረሙ መንፈሳዊ እይታዎች ያስፈልጉ ይሆን! በግለሰብ ውስጥ ያሉ ተፈጥሮአዊና በውርስ የተገኙ ባሕርያት ጽኑ ቁጥጥር ያስፈልጋቸዋል፣ ያለበለዚያ ልባዊ ቅንዓትና መልካም ዓላማዎች ወደ ክፉ ይለወጣሉ፣ ከመጠን ያለፈ ስሜት በሰብአዊ ልብ ውስጥ በስሜት እንዲወሰዱ ማድረግንና ግምቶች መሪያቸው እንዲሆኑ መፍቀድን ሊያስከትል ይችላል፡፡ {2SM 93.2}Amh2SM 93.2

    ስሜታዊ የሆኑ ሰዎች ትዕግስታቸውን እንዲያጡ የሚያደርጉ ብልሃት የጎደላቸው ቃላት እንዳይነገሩ፣ ከመጠን በላይ የሆኑ ሀሳቦች እንዳይንጸባረቁ፣ በመንፈሳዊ ስሜት ላይ ልጓም መደረግ አለበት፡፡ ጠንከር ባሉ ንግግሮች ስሜቶቻቸው በፍጥነት የሚቀሰቀሱ አንዳንድ ሰዎች አሉ፣ ሀሳባቸው አረፍተ ነገሩን ወደየአቅጣጫው ያሰፋል፤ ሁሉም ትክክል ስለሚመስላቸው አክራሪዎች ይሆናሉ፡፡ መንፈሳዊ ልምምዳቸው ትኩሳት ያለበትና በሽተኛ ይሆናል፡፡ ሰዎች ፈቃዳቸውን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሲያስገዙ እና መንፈሳቸው ትሁትና ሊስተማር የሚችል ሲሆን ጌታ በመንፈስ ቅዱሱ ያስተካክላቸውና አደጋ በሌለባቸው መንገዶች ይመራቸዋል፡፡ --Letter 66, 1894. {2SM 93.3}Amh2SM 93.3