Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለላውዶቂያውያን የተላከ መልእክት

    እግዚአብሔር ሕዝብን እየመራ ነው፡፡ የህጉ ጠባቂ አድርጎ ያስቀመጠውን ሕዝብ፣ በምድር ላይ ያለች ቤተ ክርስቲያን፣ መርጧል፡፡ ለዚህ ሕዝብ ለዓለም ሊሰጥ ያለውን ቅዱስ አደራ እና ዘላለማዊ እውነት ሰጥቷል፡፡ ይገስጻቸዋል ያርማቸዋልም፡፡ የላውዶቂያ መልእክት ታላቅ ብርሃን እያላቸው በብርሃኑ ላልተመላለሱ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች የሚሆን ነው፡፡ ታላቅ ጥሪ እንዳላቸው የሚናገሩ፣ ነገር ግን ከመሪያቸው ጋር እርምጃቸውን ካላስተካከሉና ንስሃ ካልገቡ በስተቀር ከአፉ ሊተፉ ያሉ ናቸው፡፡ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያንን ባቢሎን የሚልና የእግዚአብሔር ሕዝብ ከእሷ እንዲወጡ የሚጠራ መልእክት ከማንኛውም ሰማያዊ መልእክተኛ ወይም በእግዚአብሔር መንፈስ ከተመራ ከማንኛውም ሰብዓዊ ወኪል አይመጣም፡፡ {2SM 66.2}Amh2SM 66.2

    እውነተኛው ምስክር እንዲህ ይላል፣ «ባለጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፣ ተጎናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፣ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኩል ከእኔ ትገዛ ዘንድ አመክርሃለሁ፡፡ እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገስጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሃም ግባ፡፡ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፣ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፡፡ እኔ ደግሞ ድል እንደነሳሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፣ ድል ለነሳው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ» (ራዕይ 3፡ 18-21)፡፡ {2SM 66.3}Amh2SM 66.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents