Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አዲስ ልምምድን አደጋ ያጋጥመዋል

    አንዳንድ ነገሮችን ጠንከር ባለ መንፈስ ስለሚያዳምጡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን አዲስ የልምምድ ክፍል አደጋ ሲያገኘው ተመልክቻለሁ፡፡ አንዳንድ መምህራን በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎች አቅጣጫ ጠንካራና ውጤታማ መምህራን ቢሆኑም ሁላቸውም የተግባራዊ ሕይወት እውቀት ያላቸው እና ግራ የተጋቡ አእምሮዎችን በእርግጠኝነትና ያለ ችግር መምከር የሚችሉ ሰዎች አይሆኑም፡፡ ለውጥ ወደሚያደርግ ወደ እያንዳንዱ ቤተሰብ የግድ የሚመጣውን ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ማየት አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሁሉም ስለምናገሩት ነገር ይጠንቀቁ፤ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ የእግዚአብሔርን ሀሳብ ካላወቁ በግምት ወይም እንዲህ ይመስለኛል በማለት በፍጹም አይናገሩ፡፡ ምንም ግልጽ የሆነ የሚያውቁት ነገር ከሌለ አላውቅም ይበሉና ግለሰቡ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ይደገፍ፡፡ አንድም ሰው ቢሆን በጨለማ ውስጥ እንዳይሄድ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በብርሐን እንዳለ በብርሐን እንዲንቀሳቀስ ብዙ ጾም ጸሎት ይደረግ፡፡…Amh2SM 362.4

    የእግዚአብሔርን ሥርዓት ከማይከተሉ እና የጋለ ስሜትን ከሚቀሰቅሱ ኃይለኛና ስሜታዊ ንግግሮች የተነሳ በንብረት ላይ ከፍተኛ ክሳራ እንዳይደርስ ወይም ንብረትን መስዋዕት ማድረግ እንዳይኖር ምንም ነገር ዝብርቅርቅ ባለ ሁኔታ አይደረግ፤ ሚዛናዊ ከሆነ አእምሮ የሚመጣ ልከኝነትን፣ ተገቢ የሆነ ማሰላሰልን እና ጤናማ መርሆዎችንና ዓላማዎችን ከማጣት የተነሳ ሊገኝ የሚችል አስፈላጊ ድል ወደ ሽንፈት ይለወጣል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥበብ ያለበት አመራር ይኑር፣ ሁሉም ጠቢብና የማይታይ መካር በሆነው በእግዚአብሔር ምሪት ይንቀሳቀሱ፡፡ ሰብዓዊ የሆኑ ነገሮች የበላይነትን ለማግኘት ስለሚታገሉ የእግዚአብሔር ማህተም ያላረፈበት ሥራ ተሰርቶ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን እያንዳንዱን ነፍስ የምማጸነው ነገር ቢኖር ከልክ በላይ አጠንክሮና እምነት ጥሎ ወደ ሰብአዊ መካሪዎች ከመመልከት ይልቅ በምክር ጠቢብ ወደሆነው ወደ እግዚአብሔር እጅግ በቅንነት እንዲመለከት ነው፡፡ መንገዳችሁንና ፈቃዳችሁን ሁሉ ለእግዚአብሔር መንገድና ፈቃድ አስገዙ፡፡Amh2SM 363.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents