Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መታመን ጥቃት ደረሰበት

    አማኞች ከዚህ በፊት ለሰዎች በተሰጡት መልእክቶች ውስጥ ባሉት የእምነታችን ምሶሶዎች ላይ ያላቸውን መታመን ለመናድ ጠላት እያንዳንዱን ነገር በሥራ ላይ ያውላል፤ መልእክቶቹ በዘላለማዊ እውነት ከፍ ባለ መድረክ ላይ ያስቀመጡን እና የተመሰረቱና ለሥራው የተለየ ባሕርይ የሰጡ ናቸው፡፡ የእሥራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሰማያዊ መነሻ ያለውን እውነት እየገለጠ ሕዝቡን መርቶ አውጥቷል፡፡ ድምጹ ያኔ የተሰማ ሲሆን አሁንም እንዲህ እያለ ይሰማል፣ «ከብርታት ወደ ብርታት፣ ከጸጋ ወደ ጸጋ፣ ከክብር ወደ ክብር ወደ ፊት ሂድ፡፡» የእሥራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ መከላከያ ስለሆነ ሥራው እየጠነከረና እየሰፋ ነው፡፡Amh2SM 388.3

    እውነትን በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ በጣታቸው ጫፍ ላይ የያዙ እና መርሆዎቹን ወደ ነፍስ ቤተ መቅደስ ውስጠኛው ክፍል በማምጣት ፈንታ ጠቃሚ እውነቶችን በውጭኛው የጉባኤ ሥፍራ ያስቀመጡ ሰዎች በዚህ ሕዝብ ያለፈው ታሪክ ውስጥ ምንም ቅዱስ ነገር አያዩም፡፡ የዚህ ሕዝብ ያለፈው ታሪክ አሁን የሆኑትን እንዲሆኑ ያደረጋቸውና ከዓለም ውስጥ እውነተኛና የማይዋዥቁ ሚስዮናውያን ሠራተኞች እንዲሆኑ ያደረጋቸው ነው፡፡Amh2SM 388.4

    የወቅቱ እውነት የከበረ ነው፣ ነገር ግን ልቦቻቸው በአለቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ወድቆ ያልተሰበረ ሰዎች እውነት ምን እንደሆነ አያዩም አያስተውሉምም፡፡ የራሳቸውን አመለካከቶች የሚያስደስት ነገር በመቀበል ከተመሠረተው መሠረት ሌላ መሠረት መመስረት ይጀምራሉ፡፡ የእምነታችንን ምሶሶዎች በማስወገድ እነርሱ በቀየሱአቸው ምሶሶዎች መተካት እንደሚችሉ በማሰብ የራሳቸውን ከንቱነትና ግምት ይደልላሉ፡፡Amh2SM 389.1

    ዘመን እስካለ ድረስ ይህ እንደዚህ በመሆን ይቀጥላል፡፡ ማንኛውም ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ የነበረ ሰው በምድር ታሪክ የመዝጊያ ክስተቶች ወቅት የሚኖሩ ሰዎች ያላቸውን አቋም ማየትና ማስተዋል ይችላል፡፡ የራሳቸው አለመብቃትና ደካማነት ስለሚሰማቸው ዝም ብሎ የአምልኮት መልክ ብቻ መያዝ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ወሳኝ ግንኙነት መፍጠርን የመጀመሪያ ሥራቸው ያደርጉታል፡፡ በውስጣቸው የክብር ተስፋ የሆነው ክርስቶስ እስኪመሰረት ድረስ አርፈው ለመቀመጥ አይደፍሩም፡፡ ራስ ይሞታል፤ ኩራት ከነፍሳቸው ይወገድና የክርስቶስ የዋህነትና ደግነት ይኖራቸዋል፡፡ Manuscript 28, 1890.Amh2SM 389.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents