Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ስለ እግዚአብሔር በረከት የተያዙ የስህተት ሀሳቦች

    ብዙዎች ጥያቄ እየጠየቁና ግራ እየተጋቡ ናቸው፡፡ ይህ እየሆነ ያለበት ምክንያት በእግዚአብሔር እምነት ስለሌላቸው ነው፡፡ ለአንዳንዶች ኃይማኖታዊ ተግባራት ማለት ጥሩ ጊዜ ከማሳለፍ ትንሽ ብቻ የተሻለ ነገር ማለት ነው፡፡ ስሜቶቻቸው ሲነሳሱ እጅግ ተባርከናል ብለው ያስባሉ፡፡ አንዳንዶች ካልታወኩና ካልተረበሹ በስተቀር ተባርከናል ብለው አያስቡም፡፡ እየፈለጉት ያለው የግርግሩን ስካር ነው፤ ይህንን ካላገኙ ሁላቸውም ስህተት እንደሆኑ ወይም የሆነ ችግር እንዳለ አድርገው ይገምታሉ፡፡ {2SM 21.2}Amh2SM 21.2

    ሰዎች ብቸኛው ንጹህ ኃይማኖት በወግ አጥባቂነት ድንበር ላይ ያለ ስሜትን የሚያነሳሳ ኃይማኖት እንደሆነ እንዲያስቡ መማር የለባቸውም፡፡ አገልጋዩ በዚህ ዓይነት ተጽዕኖ ሥር ላሉት ወንጌልን ሲሰብክ ያለውን የነርቭ ጉልበት በሙሉ እንዲጠቀም ይጠበቅበታል፡፡ አንቀሳቃሽ የሆነ የሕይወት ውኃን ማዕበል አትረፍርፎ ማፍሰስ አለበት፡፡ ለሰብዓዊ ፍላጎት የሚስማሙ አነቃቂ ሽውታዎችን ማምጣት አለበት፡፡ እየበሰበሱ ያሉ ስሜቶቻቸው ካልተነቃቁ በስተቀር ግድየለሾችና ትኩረት የሌላቸው መሆን እንደሚችሉ የሚያስቡ አሉ፡፡ -- Letter 89, 1902. {2SM 21.3}Amh2SM 21.3