Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    የተንኮል ሥራ ፍሬ

    ሁሉም ከጽድቅ ጠላት ጋር በሽርክና አብረው በመስራት ሳያውቁት የእሱን ሥራ እየሰሩ ስለመሆናቸው ወይም ነፍሳትን የበለጠውን በእውነት ለማጽናት በመፈለግ ከክርስቶስ ጋር በመገናኘት የእሱን ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን በመፈተሸ ምን አይነት ከባቢ አየር ነፍሳቸውን እንደሚከብ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ {2SM 70.1}Amh2SM 70.1

    ሰይጣን ወንድም በወንድሙ ላይ ያለውን መታመን ለማዳከምና እውነትን እናምናለን በሚሉት መካከል አለመስማማትን ለመዝራት ማንንም የሥራ አጋሩ ማድረግ ሲችል ደስ ይለዋል፡፡ ሰይጣን ዓላማዎቹን በተሳካ ሁኔታ መፈጸም የሚችለው በክርስቶስ መንገድ በማይሄዱና በማይሰሩ ግን የክርስቶስ ወዳጆች ነን በሚሉ ሰዎች አማካይነት ነው፡፡ ጌታ ለወቅቱ ካለው የተለየ ሥራ በአእምሮና በልብ የሚርቁ ሰዎች፣ ነፍሳት የእሱን የማስጠንቀቂያ ቃላት እንዲሰሙ በመምራት በእምነት ለማጽናት ከእሱ ጋር የማይተባበሩ፣ የክርስቶስ ጠላት ሥራን እየሰሩ ናቸው፡፡ {2SM 70.2}Amh2SM 70.2

    ሚስዮናዊ ሥራ እየሰሩ በመምሰል ከቤት ወደ ቤት በመሄድ የአለመተማመንንና የጥርጣሬን ዘር መዝራት እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ እያንዳንዱ ዘር በፍጥነት ይበቅልና የእሱን መልእክት ለሕዝብ ለማድረስ በያዙ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ላይ እምነት ማጣትን ይፈጥራል፡፡ እግዚአብሔር በባሪያዎቹ አማካይነት ሲናገር፣ አስቀድሞ ተዘርቶ የነበረው ዘር [የአለመተማመንና የጥርጣሬ] ወደ መራራነት ሥር አድጓል፡፡ ቃሉ በማይሰሙ ወይም ምላሽ በማይሰጡ ልቦች ላይ ይወድቃል፡፡ ማንኛውም ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ኃይል ነፍስ ጋ መድረስ አይችልም፡፡ {2SM 70.3}Amh2SM 70.3

    ለእነዚህ ነፍሳት ተጠያቂው ማን ነው? የጌታን ቃል እንዳይሰሙ የከለከለውን ያንን የመራርነት መርዘኛ ሥር ማን ያጠፋል? ጥሩ እህት ወይም ወንድም መጥፎ ዘር ተከለ፣ ነገር ግን ከዚህ የተነሳ አደጋ ላይ የወደቀውን ነፍስ እንዴት አድርጎ መመለስ ይችላል? በእግዚአብሔር ሰራተኞች የተስፋ፣ የእምነትና የመታመን ቃላትን በመናገር ለእግዚአብሔር ክብር ጥቅም ላይ መዋል ይችል የነበረው ምላስ ነፍስን ከኢየሱስ ክርስቶስ መልሷል፡፡ የኢየሱስን ቃላት የናቁ፣ ድምጹን ለመስማትና ለመለወጥ እምቢ ያሉት በክፉ ሀሳቦችና ክፉ በመናገር እርሾ ሌሎች አእምሮዎችን አኮምጥጠዋል፡፡ {2SM 70.4}Amh2SM 70.4

    ይህ የጌታ ዝግጅት ቀን ነው፡፡ አሁን አለማመንን እና ሀሜትን ለመናገር ጊዜ የለንም፣ አሁን የሰይጣንን ሥራ ለመሥራት ጊዜ የለም፡፡ እያንዳንዱ ሰው የቅንዓትን፣ የምቀኝነትንና የመለያየትን ዘር በመዝራት የሌሎችን እምነት ከማናጋት ይቆጠብ፣ እግዚአብሔር ቃላቱን ይሰማል፡፡ እሱ የሚፈርደው አዎን ወይም አይደለም በሚሉ ማረጋገጫዎች ሳይሆን የአንድ ሰው ተግባር በሚያፈራው ፍሬ ነው፡፡ «ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ» (ማቴ. 7፡ 20)፡፡ የተዘራው ዘር የመከሩን ዓይነት ይወስናል፡፡ --Manuscript 32a, 1896. {2SM 71.1}Amh2SM 71.1