የትንቢት እርግጠኝነት
እግዚአብሔር እንደሚፈጸም በትንቢታዊ ታሪክ ውስጥ የገለጸው ተፈጽሟል፣ ወደ ፊት የሚመጣውም ሁሉ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ይመጣል፡፡ የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነው ዳንኤል በስፍራው ይቆማል፡፡ ዮሐንስም በስፍራው ይቆማል፡፡ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንባሳ ትንቢትን ለሚያጠኑ ተማሪዎች የዳንኤልን መጽሐፍ ከፍቶላቸዋል፣ በመሆኑም ዳንኤል በስፍራው ቆሟል፡፡ በመፈጸሚያቸው ጫፍ ላይ ያለን ሰዎች ማወቅ ስላለብን ታላላቅና ከባባድ ክስተቶች እግዚአብሔር በራዕይ የገለጠለትን ምስክርነት ያስተላልፋል፡፡ {2SM 109.1}Amh2SM 109.1
በታሪክና በትንቢት ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል በእውነትና በውሸት መካከል ለረዥም ጊዜ የቀጠለውን ግጭት ያሳያል፡፡ ይህ ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩ ነገሮች ይደገማሉ፡፡ የቀድሞዎቹ ተጋድሎዎች ይነቃቃሉ፣ አዳዲስ ንድፈ ሀሳቦች በቀጣይነት ይነሳሉ፡፡ ነገር ግን በእምነታቸውና ትንቢትን በመፈጸም ረገድ የአንደኛውን የሁለተኛውንና የሶስተኛውን መላእክት መልእክቶች በማወጅ ድርሻቸውን የተወጡት የእግዚአብሔር ሕዝቦች የት እንደሚቆሙ ያውቃሉ፡፡ ከንጹህ ወርቅ የበለጠ ውድ የሆነ ልምምድ አላቸው፡፡ የመጀመሪያውን መታመናቸውን እስከ መጨረሻ አጽንተው በመያዝ እንደ አለት ጸንተው መቆም አለባቸው፡፡{2SM 109.2}Amh2SM 109.2
የሚለውጥ ኃይል የሶስተኛውን መልአክ መልእክት እንደተከተለው ሁሉ የአንደኛውንና የሁለተኛውን መላእክት መልእክቶችንም አጅቦአቸዋል፡፡ በሰብአዊ አእምሮዎች ውስጥ ዘለቄታ ያላቸው ጽኑ እምነቶች ተፈጥረዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት ነጥብ በነጥብ ያጠኑ ነበር፡፡ ሌሊቱን በሙሉ ቃሉን በትጋት በመመርመር ያሳልፉ ነበር፡፡ እውነትን እንደ ተደበቀ ሀብት ፈለግነው፡፡ ጌታ ራሱን ገለጠልን፡፡ በትንቢቶች ላይ ብርሃን በራ፣ እኛም መለኮታዊ መመሪያ እንደተቀበልን አወቅን፡፡. . . {2SM 109.3}Amh2SM 109.3
ከታላቁ ተስፋ መቁረጥ በኋላ በሙሉ ልባቸው ቃሉን ለመፈለግ ራሳቸውን ያዘጋጁት ጥቂት ነበሩ፡፡ ነገር ግን ጥቂት ነፍሳት በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ለመቅረትና እግዚአብሔር እንደመራቸው ለመካድ አልፈለጉም፡፡ ለእነዚህ ሰዎች እውነት ነጥብ በነጥብ ተገለጠላቸው፣ ይህ ደግሞ እጅግ ከተቀደሱ ትዝታዎቻቸውና ርኅራኄዎቻቸው ጋር ተያይዞ ነበር፡፡ እውነትን ይፈልጉ የነበሩት ሰዎች ከባህርያቸውና ከፍላጎታቸው ጋር ክርስቶስ ተለይቶ መታየት ተግባራዊ እንደሆነ ተሰማቸው፡፡ እውነት በትህትና ውበት፣ በኃይል ከብሮና ተስፋ ከመቁረጥ በፊት በማይታወቅ መተማመኛ እንዲበራ ተደረገ፡፡ ከዚያ በኋላ መልእክቱን በአንድነት ማወጅ ቻልን፡፡ {2SM 109.4}Amh2SM 109.4
ነገር ግን እምነታቸውንና ልምምዳቸውን አጽንተው ካልያዙት መካከል ታላቅ ግራ መጋባት ነበር፡፡ እያንዳንዱ ሊታሰብ የሚችል አመለካከት እንደ እውነት መልእክት ቀርቦ ነበር፤ ነገር ግን የጌታ ድምጽ «እኔ አልላኳቸውምና አትመኑአቸው” የሚል ነበር፡፡ {2SM 110.1}Amh2SM 110.1
ከእግዚአብሔር ጋር በጥንቃቄ ተራመድን፡፡ መልእክቱ ለዓለም ሊሰጥ ነበር፣ ይህ የወቅቱ ብርሃን ከእግዚአብሔር የመጣ ልዩ ስጦታ እንደሆነ አወቅን፡፡ ይህን ስጦታ ማጋራት የእግዚአብሔር መብት ነበር፡፡ ተስፋ የቆረጡትና አሁንም እውነትን እየፈለጉ የነበሩት የእርሱ ሕዝብ ለእነርሱ የተነገራቸውን ለዓለም እንዲነግሩ ደረጃ በደረጃ ተመሩ፡፡ ትንቢታዊ አዋጆች መደገም ነበረባቸው፣ ለድነት አስፈላጊ የሆነ እውነትም መታወቅ ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ ሥራው አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ተንቀሳቀሰ፡፡ ብዙ ጊዜ አድማጮቹ መልእክቱን ለመረዳት የማይቻል ነው በማለት መቀበል እምቢ አሉ፣ በተለይ የሰንበት ጥያቄን በተመለከተ ጽኑ የሆነ ግጭት ተጀመረ፡፡ ነገር ግን ጌታ የእርሱን መገኘት ግልጽ አደረገ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከዓይናችን ክብሩን የጋረደብን መጋረጃ ገለል ብሎልን ነበር፡፡ እርሱን በከፍታና በቅዱስ ቦታ ተመለከትነው፡፡ {2SM 110.2}Amh2SM 110.2
መንፈስ ቅዱስ ከዚህ በፊት በነበሩ ዘመናት ባሪያዎቹ እንዲያውጁት ያነሳሳቸውን እውነት ወደ ጎን እንዲተው ጌታ አሁን አእምሮዎችን አይመራም፡፡ {2SM 110.3}Amh2SM 110.3
ባለፉት ጊዜያቶች የነበሩ ሰዎች እንደፈለጉት ሁሉ ብዙዎች በታማኝነት ብርሃንን ለማግኘት ቃሉን ይመረምራሉ፤ በቃሉ ውስጥም ብርሃንን ያያሉ፡፡ ነገር ግን በልምምዳቸው እነዚህ የማስጠንቀቂያ መልእክቶች መጀመሪያ በተሰጡበት ወቅት በነበሩት ቦታዎች አላለፉም፡፡ ይህ ልምምድ ስላልነበራቸው ለእኛ እንደ መንገድ ዳር ምልክት የሚያገለግሉትንና ልዩ ሕዝብ እንድንሆን ያደረጉንን እውነቶች ዋጋ ብዙዎች አያደንቁም፡፡ ጥቅሶቹ የሚሉትን ነገር በትክክል ሥራ ላይ ስለማያውሉት ትክክል ያልሆኑ ንድፈ ሀሳቦችን ያዘጋጃሉ፡፡ ብዙ ጥቅሶችን መጥቀሳቸውና እውነት የሆነ ብዙ ነገር ማስተማራቸው እውነት ነው፤ ነገር ግን ወደ ስህተት ድምዳሜ ለመምራት እውነት ከስህተት ጋር ተቀላቅሏል፡፡ ሆኖም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ከራሳቸው ንድፈ ሀሳቦች ጋር መሸመን ስለሚችሉ ቀጥ ያሉ የእውነት ሰንሰለት እንዳላቸው ያስባሉ፡፡ በመልእክቶቹ አነሳስ ላይ ልምምድ ያልነበራቸው ብዙዎች እነዚህን የስህተት ንድፈ ሀሳቦች ይቀበሉና ወደ ፊት ከመሄድ ይልቅ ወደ ኋላ ወደሚወስዱ መንገዶች ይመራሉ፡፡ {2SM 110.4}Amh2SM 110.4