Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    “ያመንኩትን አውቃለሁ”

    ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለበርካታ ሌሊቶች እንቅልፍ ማግኘት የቻልኩ ቢሆንም ማንቀላፋት የቻልኩት ለሁለት ሰዓታት ብቻ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ በዙሪያዬ ጨለማ ይሰበሰብ ነበር፤ ነገር ግን ጸሎት አደርግኩና ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ያለውን ብዙ የሆነ ጣፋጭ መጽናናት ተገነዘብኩ፡፡ «ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፣ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል (ያዕቆብ 4፡ 8) እና «ጠላት እንደ ጎርፍ ሲመጣ የእግዚአብሔር መንፈስ አርማውን ያነሳበታል» (ኢሳ. 59፡ 19) የሚሉ ተስፋዎች ለእኔ ተፈጻሚ ሆነዋል፡፡ ሙሉ በሙሉ በጌታ ብርሃን ነበርኩ፡፡ ኢየሱስ በቅድስና አጠገቤ ስለነበር የተሰጠኝ ጸጋ በቂ ሆነ አገኘሁት፤ ነፍሴ እግዚአብሔርን ስለጠበቀች ለወደደኝና ራሱን ለሰጠኝ ለእርሱ በምስጋና ተሞልቼ ነበር፡፡ ከሙሉ ልብ እንዲህ ማለት እችላለሁ፣ «ያመንኩትን አውቃለሁ” (2ኛ ጢሞ. 1፡ 12)፡፡ «ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው» (1ኛ ቆሮ. 10፡ 13)፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ከአሸናፊዎች በላይ በመሆን ከፍ ያለ ቦታ ይዣለሁ፡፡ Amh2SM 241.2

    በእኔ ሥቃይ ውስጥ የእግዚአብሔር ዓለማ ምን እንደሆነ ማንበብ አልችልም፣ ነገር ግን እርሱ የተሻለው ምን እንደሆነ ስለሚያውቅ ነፍሴን፣ አካሌንና መንፈሴን ለታማኝ ፈጣሪዬ አሳልፌ እሰጣለሁ፡፡ «ያመንሁትን አውቃለሁና፣ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቻለሁ» (2ኛ ጢሞ. 1፡ 12)፡፡ ነፍሳችን የበለጠ እምነት፣ የበለጠ ፍቅር፣ የበለጠ ትዕግሥት፣ እና በሰማያዊው አባታችን ላይ የበለጠ ፍጹም መታመን እንዲኖረው አስተምረንና አሰልጥነን ቢሆን ኖሮ በየቀኑ በዚህ ሕይወት ጦርነት ውስጥ ስናልፍ የበለጠ ሰላምና ደስታ ሊኖረን ይችል እንደነበር አውቃለሁ፡፡ Amh2SM 242.1

    ከኢየሱስ ክንዶች ወጥተን ስንጨነቅና ስናዝን ጌታ ደስ አይለውም፡፡ ፀጥታ ያለበት መጠበቅና መንቃት የበለጠ ያስፈልጋል፡፡ በትክክለኛ መስመር ላይ እንዳልሆንን ካልተሰማን እና ለሁኔታው ገጣሚ የሚሆን የሆነ ምልክት በውስጣችን ካልፈለግን በስተቀር እናስባለን፤ ነገር ግን መተማመን ከስሜት ሳይሆን ከእምነት ነው፡፡Amh2SM 242.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents