Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ታሪክ ተደገመ

    እኔና ባለቤቴ በእግዚአብሔር ፈቃድ ድርሻችንን እንድንወጣ በተጠራንበት ሥራ፣ ሥራው ከተጀመረበት በ1843 እና 1844 ጀምሮ፣ እቅድ ሲያቅድልንና መንገዶችን ሲያሳየን የነበረው ጌታ ነበር፣ እቅዶቹን ወደ ሥራ የተረጎመው ደግሞ በሕያዋን ወኪሎቹ አማካይነት ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ የውሸት መንገዶችን እንድናይ ተደርገን ነበር፣ እንድንሰራ ከተሰጠን ሥራ ጋር ግንኙነት ባላቸው አስቸጋሪ እቅዶች ሁሉ ውስጥም እውነተኛና አደጋ የሌለባቸው መንገዶች በግልጽ ተብራርተውልን ስለነበር የሰይጣን ወጥመዶችን በተመለከተም ሆነ የእግዚአብሔርን መንገዶች በተመለከተ ማይም እንዳልነበርኩ እውነቱን መናገር እችላለሁ፡፡ እንዳንታለልም ሆነ ሌሎችን እንዳናታልል ወደ ትኩረታችን የመጡ ንድፈ ሀሳቦችን መልካምነታቸውንና ጉድለቶቻቸውን ከእግዚአብሔር ቃል በሚበራ ብርሃን እና እግዚአብሔር በቃሉና በምስክርነቶች አማካይነት በገለጠልኝ ነገሮች አማካይነት በመመዘን መመርመር ስለነበረብን በምርምራችን ውስጥ እንዲመራን ከእግዚአብሔር በሆነው ጥበብ በመደገፍ እያንዳንዱን የአእምሮ ኃይል ሥራ ላይ ማዋል ነበረብን፡፡ መንገዳችንን እና ፈቃዳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን በመስጠት ለእርሱ እርዳታ ከልባችን ተማጸንን፤ እንፈልግ የነበረው በከንቱ አልነበረም፡፡ ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር በተገናኘ ሁኔታ የነበረኝ የብዙ አመታት አስጨናቂ ልምምድ ከሁሉም አይነት የሀሰት እንቅስቃሴዎች ጋር አስተዋውቆኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ከምከተለው መልእክት ጋር ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተልኬ ነበር፣ «በዚያ ቦታ የምትሰሪልኝ ሥራ አለ፤ ከአንቺ ጋር እሆናሉ፡፡» አጋጣሚው ሲመጣ የውሸት ሕልሞችና ራዕዮች ለነበሩአቸው እንድነግር ጌታ መልእክት ሰጠኝ፣ በክርስቶስ ብርታት በጌታ ትዕዛዝ ምስክርነቶቼን አስተላለፍኩ፡፡ እንደ እነርሱ አመለካከት የእግዚአብሔርን ሥራ እየተቃወምኩ ስለነበር ከእግዚአብሔር ናቸው ያሉአቸው እጅግ አሰቃቂ የሆኑ ትችቶች (ውንጀላዎች) ተወርውረውብኛል፡፡ የአንተ ኣና እንደተነበየችው በእኔ ላይ አሰቃቂ የሆኑ መቅሰፍቶች እንደሚወርዱብኝ ተናገሩ፤ ነገር ግን ሰማያዊ መላእክት እንደሚጠብቁኝ በፍጹም በማወቅ በሰላም አለፍኩ፡፡ {2SM 75.1}Amh2SM 75.1

    ባለፉት አርባ አምስት አመታት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተግሳጽ መልእክቶች እንዳሏቸው የሚናገሩ ሰዎችን አገኝ ነበር፡፡ ይህኛው ኃይማኖታዊ አክራሪነት ክፍል ከ1844 ጀምሮ በተደጋጋሚ ተነስቶ ነበር፡፡ ውሸትን ለማጽናት ሰይጣን በብዙ መንገዶች ሰርቶ ነበር፡፡ በእነዚህ ራዕዮች ከተነገሩ ነገሮች አንዳንዶቹ ተፈጸሙ፤ ነገር ግን ብዙ ነገሮች- የክርስቶስን የመምጫ ጊዜ፣ የምህረት በር መዘጋትን እና ወደ ፊት የሚሆኑ ክስተቶችን በተመለከተ የአንተና የኣና ትንቢቶች እንደሆኑ ሁሉ ፍጹም ውሸትነታቸው ተረጋገጠ፡፡ ነገር ግን አረፍተ ነገሮችን በማጣመምና ሌላ ትርጉም በመስጠት ለስህተታቸው ሰበብ ይፈልጋሉ፣ እያታለሉና እየተታለሉ በዚህ መንገድ ይሄዳሉ፡፡ {2SM 75.2}Amh2SM 75.2

    መጀመሪያ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ በሰራ ጊዜ ራዕዮችን እንደሚያዩ ከሚናገሩ ሰዎች ጋር እንደምገናኝ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር እንድታለል እንደማይፈቅድ እንዳይ ተደርጌ ነበር፡፡ የእኔ ሥራ ይህን ውሸት ማጋለጥና በጌታ ስም መገሰጽ ነበር፡፡ መጨረሻው እየቀረበ ሲሄድ እነዚህን መገለጦች የበለጠ እንደማይ ተነግሮኝ ነበር፡፡ {2SM 76.1}Amh2SM 76.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents