Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሥራና የደሞዝ እድሎች ሲነጻጸሩ

    የጌታ አገልጋይ በመሆን ከሚገኝ ክብር ይልቅ ስለሚከፈላቸው ደሞዝ የበለጠ የሚያስቡ ሰዎች፣ ደሞዝ ስለሚከፈላቸው ራሳቸውን ለማስደሰት ሥራ የሚሰሩ ሰዎች፣ በሥራቸው ውስጥ ራስን መካድንና ራስን መስዋዕት ማድረግን አያመጡም፡፡ በመጨረሻ የተቀጠሩት ሙያተኞች «የሚገባችሁን ትቀበላላችሁ” (ማቴ. 20፡7) የሚለውን የባለቤቱን ቃል አመኑ፡፡ የሚገባቸውን ሁሉ እንደሚቀበሉ ስላወቁ እና በሥራቸው ውስጥ እምነትን ስላስገቡ የመጀመሪያ ቦታ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ቀኑን ሙሉ ሲሰሩ የነበሩትም በሥራቸው ውስጥ የፍቅርና የመታመን መንፈስ አሳይተው ቢሆን ኖሮ የመጀመሪያዎች ሆነው ይቀጥሉ ነበር፡፡ Amh2SM 182.1

    እግዚአብሔር የተሰራውን ሥራ የሚገምተው ሥራው በተሰራበት መንፈስ ነው፡፡ ወደ እርሱ በትሁት እምነት የሚመጡትንና ትእዛዛቱን የሚታዘዙትን ተናዛዥ ኃጢአተኞች በረፋድ ሰዓት ይቀበላቸዋል፡፡ Amh2SM 182.2

    ክርስቶስ በአገልግሎቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ጌታቸው እውነተኛ በሆነ መንገድ እንደማይከፍላቸው በመቁጠር ለምን ይህን ያህል አልተከፈለኝም በማለት እንዳይከራከሩ ያስጠነቅቃቸዋል፡፡ አጉረምራሚዎች አለን ለሚሉት ቅሬታ ርኅራኄ እንደማያገኙ ለማሳየት ይህን ምሳሌ ሰጠ፡፡--Manuscript 87, 1899.Amh2SM 182.3

    ያለማቋረጥ ከፍተኛ ደሞዝ ለማግኘት ለሚፈልግ እና እግዚአብሔር እንዲሰራ ከሰጠው ሥራ እንዲርቅ ለሚያደርገው ፈተና ለሚሸነፍ ነፍስ እውነተኛ የሆነ ብልጽግና በፍጹም አይመጣለትም፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ ካልመራ በስተቀር ማንኛውም ሰው፣ ወይም ቤተሰብ፣ ወይም ማንኛውም ድርጅት ወይም ተቋም እውነተኛ የሆነ ብልጽግና ሊኖረው አይችልም፡፡--Letter 2, 1898. (Tract “To the Leading Men in Our Churches,” p. 4.)Amh2SM 182.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents