Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ሊከፈል የሚገባውን ያህል ላለመጠየቅ

    ክርስቶስ ከሁሉም «እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፡- ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና፣ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” (ማቴ 11፡ 28-30)፡፡ ሁሉም የክርስቶስን ቀንበር ቢሸከሙ ኖሮ፣ ሁሉም በእርሱ ትምህርት ቤት እርሱ የሚያስተምራቸውን ትምህርቶች ቢማሩ ኖሮ፣ በሕክምና አገልግሎት አማካይነት የሚደረገውን የወንጌል ሚስዮናዊነት ሥራ በብዙ ቦታዎች ለመመስረት በቂ ገንዘብ ይኖር ነበር፡፡ Amh2SM 180.1

    ማንም ቢሆን «ሕጉ የሚያዘውን ያህል ደሞዝ ካገኘሁ ይህን ሥራ እሰራለሁ፡፡ ያን ያህል የማይከፈለኝ ከሆነ ሥራውን አልሰራም” አይበል፡፡ ይህን የሚሉ ሰዎች የክርስቶስን ቀንበር አልተሸከሙም፤ የእርሱን የዋህነትና ትህትና እየተማሩ አይደሉም፡፡. . .Amh2SM 180.2

    በእግዚአብሔር ፊት ያለንን ዋጋ የሚጨምረው በዓለም ሀብት ሀብታም ሆኖ መገኘት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር እውቅና የሚሰጣቸውና የሚያከብራቸው ሰዎች የዋሃንና ለኃጢአታቸው የሚጸጸቱ ናቸው፡፡ ኢሳይያስ ምዕራፍ ሃምሳ ሰባትን ያንብቡ፡፡ ይህን ምዕራፍ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ብዙ የሚጠቅም መልእክት ስላለው በጥንቃቄ ያጥኑ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ላይ ምንም ተጨማሪ አስተያየት አልሰጥም፡፡--Letter 145, 1904.Amh2SM 180.3