Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከመለኮታዊ ወኪሎች ጋር መተባበር

    በምድር ላይ ያሉት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ለሰዎች ድነት ከመለኮታዊ ወኪሎች ጋር መተባበር ያለባቸው ሰብዓዊ ወኪሎች ናቸው፡፡ ራሳቸውን ከእሱ ጋር ላገናኙት ነፍሳት ክርስቶስ እንዲህ ይላል፣ «ከእኔ ጋር አንድ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና” (1ቆሮ. 3፡9)፡፡ እግዚአብሔር ታላቁና የማይታይ ተዋናይ ነው፤ ሰው ዝቅተኛና የሚታይ ወኪል ነው፣ ምንም አይነት መልካም ነገር ማድረግ የሚችለው ከሰማያዊ ወኪሎች ጋር ሲተባበር ብቻ ነው፡፡ ሰዎች መለኮታዊ ወኪልን መለየት የሚችሉት መንፈስ ቅዱስ ለአእምሮአቸው መረዳትን ሲሰጥ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ሰው ከሰማይ ጋር እንዳይተባበር ለማድረግ ሰይጣን አእምሮን ከመለኮታዊ ነገሮች ወደ ሰብዓዊ ነገሮች ለመመለስ ያለማቋረጥ በመሻት ላይ ነው፡፡ ሰዎች በሰው እንዲታመኑና ሥጋን ክንዳቸው እንዲያደርጉ በመምራት እምነታቸው በእግዚአብሔር ላይ እንዳይጸና ለማድረግ ትኩረትን ወደ ሰብዓዊ ፈጠራዎች ይመልሳል፡፡ {2SM 123.1}Amh2SM 123.1

    «የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!” (ማቴ. 6፡22፣23)፡፡ {2SM 123.2}Amh2SM 123.2

    ብርሃናችን ጨለማ ሆኖ እንዴት ለዓለም ብርሃን መሆን እንችላለን? {2SM 123.3}Amh2SM 123.3

    የግል መዳናችን ሥራ ከመለኮታዊ ኃይሎች ጋር ባለን ትብብር ላይም ይደገፋል፡፡ እግዚአብሔር የሞራል ኃይሎችንና ኃይማኖታዊ ተጋላጭነቶችን አጋርቶናል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ እንድንችል ለኃጢአታችን ካሣ እንዲሆን ልጁን ሰጥቷል፡፡ እኛ የእርሱን ምሳሌ መከተል እንድንችል ኢየሱስ ራስን የመካድና የመስዋዕትነት ኑሮ ኖረ፡፡ እርዳታ በሚያስፈልግበት ቦታ ሁሉ በክርስቶስ ቦታ እንዲሆን መንፈስ ቅዱስን ሰጥቷል፡፡ መለኮታዊ ኃይልን ከሰብአዊ ጥረቶች ጋር ለማጣመር ሰማያዊ ኃይሎችን ሥራ ላይ ያውላል፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ስጦታ መቀበል አለብን፣ ንስሃ መግባትና በክርስቶስ ማመን አለብን፡፡ መንቃት አለብን፣ መጸለይ አለብን፣ እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚፈልግብንን ነገሮች መታዘዝ አለብን፡፡ ለክርስቶስ ብለን ራስን መካድንና ራስን መስዋዕት ማድረግን መለማመድ አለብን፡፡ ከእርሱ ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት በመፍጠር ወደ ክርስቶስ ማደግ አለብን፡፡ በሰው እንድንታመን ወይም ከሰብአዊ መስፈርቶች ጋር እንድንስማማ ለማድረግ አእምሮን ከእግዚአብሔር የሚመልስ ማንኛውም ነገር በራሳችን የድነት ሥራ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር እንዳንተባበር ይከለክላል፡፡ ሕዝቡ ከአህዛብ ጋር ሕብረት እንዳይፈጥር እግዚአብሔር የከለከለው ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ «በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትሄድባት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ” (ዘጸ. 34፡12)፡፡ እንዲህ አለ፣ «እንዳይከተለኝ ሌሎችንም አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና የእግዚአብሔርም ቍጣ ይነድድባችኋል፥ ፈጥኖም ያጠፋችኋል» (ዘዳ. 7፡4)፡፡ ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ከማያምኑ ሰዎች ጋር የሚፈጥሩትን ሕብረት በተመለከተ ይህ መርህ ሥራ ላይ ይውላል፡፡ {2SM 123.4}›Amh2SM 123.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents