Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 13—ክርስቲያኖች የምስጢር ማህበራት አባላት መሆን አለባቸውን?

    [በዚህ ርዕስ በ1893 ዓ.ም ከታተመው ላይ እንደገና የታተመ.]

    «ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። ስለዚህም ጌታ፡- ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፡- እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል” (2ቆሮ. 6፡14-18)። {2SM 121.1}Amh2SM 121.1

    «ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ” (2ቆሮ. 6፡14) የሚለው የጌታ ትዕዛዝ የሚያመለክተው ክርስቲያኖች ከማያምኑ ጋር ስለሚፈጥሩት ጋብቻ ብቻ ሳይሆን ሁለቱም ወገኖች የቀረበ ግንኙነት በመፍጠር በመንፈስና በድርጊት ወደ መጣጣም ሊመጡ የሚችሉባቸውን ሕብረቶች በሙሉ ነው፡፡ እሥራኤላውያን ከጣዖት አምላኪዎች ራሳቸውን እንዲለዩ እግዚአብሔር ልዩ መመሪያ ሰጥቷቸው ነበር፡፡ ከአህዛብ ጋር መጋባትም ሆነ ምንም ዓይነት ሕብረት መፍጠር የለባቸውም፡፡ «በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትሄድባት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፡፡ ነገር ግን መሠዊያዎቻቸውን ታፈርሳላችሁ፥ ሐውልቶቻቸውንም ትሰብራላችሁ፥ የማምለኪያ ዓፀዶቻቸውንም ትቈርጣላችሁ፡፡ ስሙ ቀናተኛ የሆነ እግዚአብሔር ቅንዓት ያለው አምላክ ነውና ለሌላ አምላክ አትስገድ” (ዘጸ. 34፡12-14)፡፡ {2SM 121.2}Amh2SM 121.2

    «ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና በምድር ፊት ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መረጠህ። እግዚአብሔርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ስለ በዛችሁ አይደለም እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ጥቂቶች ነበራችሁና፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አዳናችሁ። አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ” (ዘዳ. 7፡6-9)፡፡ {2SM 122.1}Amh2SM 122.1

    ደግሞ በነቢዩ ኢሳይያስ አማካይነት ጌታ እንዲህ ይላል፡- «አሕዛብ ሆይ፥ እወቁና ደንግጡ እናንተም ምድራችሁ የራቀ ሁሉ፥ አድምጡ ታጠቁም፥ ደንግጡ ታጠቁ ደንግጡ። ተመካከሩ፥ ምክራችሁም ይፈታል ቃሉን ተናገሩ፥ ቃሉም አይጸናም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና። እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ እንዲህ ተናገረኝ፥ በዚህም ሕዝብ መንገድ እንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ፥ እንዲህም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ፡- ዱለት ነው በሚሉት ሁሉ፡- ዱለት ነው አትበሉ መፈራታቸውንም አትፍሩ፥ አትደንግጡ። ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን” (ኢሳ. 8፡9-13)፡፡ {2SM 122.3}Amh2SM 122.2

    ክርስቲያኖች ከፍሪ ማሶኖች ጋር ወይም ከሌሎች የምስጢር ማሕበራት ጋር ሕብረት መፍጠር ትክክል ነው ወይስ አይደለም ብለው የሚጠይቁ አሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ ያላቸው ሁሉ ከላይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች ልብ ይበሉ፡፡ ክርስቲያኖች ከሆንን በሁሉም ቦታ ክርስቲያኖች መሆን አለብን፣ የእግዚአብሔር ቃል በሚያስቀምጥልን መስፈርት መሠረት ክርስቲያኖች ሊያደርገን የተሰጠንን ምክር መገንዘብና ልብ ማለት አለብን፡፡ {2SM 122.4}Amh2SM 122.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents