Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    አክራሪነት (ወግ አጥባቂነት) እንደ ገና ሊታይ ነው

    ወግ አጥባቂነት በተለያዩ መንገዶች እንደገና እንደሚታይ ከብዙ ጊዜ በፊት አውቄ ስለነበር አብዛኛው ሕዝባችን እንዲያውቃቸው ከእነዚህ የጥንት ልምምዶች መካከል አንዳንዶቹን እንዴት በድጋሚ ለሕትመት ማብቃት እንደሚቻል ጥናት ሳደርግ ነበርኩ፡፡ አንዳንዶች ለመድረስና ለመለማመድ እጅግ የሚፈጥኑባቸውን እንግዳ ተግባሮችንና እንቅስቃሴዎችን ሁሉ ለመራቅ ቃሉን በመናገር አቋማችንን ማጽናት ያስፈልገናል፡፡ በሥራችን ውስጥ ግራ መጋባት እንዲገባ ብንፈቅድ ኖሮ ተግባራችንን መሆን የሚገባውን ያህል ማከናወን አንችልም ነበር፡፡. . . {2SM 44.1}Amh2SM 44.1

    ክርስቶስ በምድር ላይ ያገለግል በነበረባቸው አመታት አዳኙና ደቀ መዛሙርቱ ያከናውኑ የነበሩትን ሥራ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሴቶች አግዘዋል፡፡ ይህን ሥራ ይቃወሙ የነበሩ ሰዎች በእነዚህ ሴቶች ባሕርይ ውስጥ ከተለመደው ሥርዓት ውጭ የሆነ ነገር ማግኘት ቢችሉ ኖሮ ሥራው ወዲያውኑ እንዲዘጋ ያደርጉ ነበር፡፡ ነገር ግን ሴቶች ከክርስቶስና ከደቀ መዛሙርት ጋር አብረው በሚሰሩበት ጊዜ መላው ሥራ ይከናወን የነበረው ከጥርጣሬ ጥላ በላይ መሆን በሚችልበት ከፍ ባለ ደረጃ ነበር፡፡ ለማንኛውም ክስ መንገድ የሚከፍት አጋጣሚ ሊገኝ አይችልም ነበር፡፡ የሁሉም አእምሮዎች ወደ ግለሰቦች ሳይሆን ወደ ቅዱሳን መጻሕፍት ተመርተው ነበር፡፡ እውነት ሁሉም ሊያስተውሉ በሚችሉበት ሁኔታ በማስተዋልና በግልጽ ታውጆ ነበር፡፡ {2SM 44.2}Amh2SM 44.2

    በሕዝባችን መካከል ማንኛውም የአክራሪነት (የወግ አጥባቂነት) ተፈጥሮ ያለው ነገር እንዳይኖር በጣም እፈራለሁ፡፡ መቀደስ ያለባቸው እጅግ ብዙዎች አሉ፣ ነገር ግን መቀደስ ያለባቸው ለእውነት መልእክት በመታዘዝ ነው፡፡... {2SM 44.3}Amh2SM 44.3

    በመካከላችን ያሉ በቀላሉ ስሜቶቻቸው የሚነሳሱ አካላት በእውነት ልንደርሳቸው በምንሻቸው ሰዎች ዘንድ ሊኖረን የሚችለውን መልካም ተጽዕኖ ሊያበላሽ በሚችል ሁኔታ ራሳቸውን እንዲያሳዩ ልንፈቅድ አንችልም፡፡ የተለየ ሕዝብ ሆነን መኖር በጀመርንበት በቀድሞዎቹ ዘመናት የነበሩ ወግ አጥባቂ አካላትን እንግዳ የሆኑና ክፉ ሥራዎቻቸውን ከማወቃቸው የተነሳ የማያምኑ ሰዎች ስለ አድቬንቲስቶች የነበራቸውን መጥፎ አሻራ ተቋቁመን ለማለፍ አመታትን ፈጅቶብናል፡፡ --Manuscript 115, 1908. {2SM 44.4}Amh2SM 44.4