Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ግርግር ከሰፈነበት ውካታና ጫጫታ ጋር የሚደረግ አምልኮ

    እግዚአብሔር የራሱን ሀሳብና ዓላማ በመፈጸም ረገድ በራሱ በተመረጡ መሳሪያዎች የሚፈጽመውን ሥራ ለመገመት እጅግ ከባድ ነው፡፡ በኢንዲያና በመሆን ላይ እንዳሉ የተገለጹልኝ ነገሮች የምህረት በር ከመዘጋቱ በፊት ትንሽ ቀደም ብለው እንደሚሆኑ ጌታ አሳይቶኛል፡፡ እያንዳንዱ ስድ ነገር ይታያል፡፡ በከበሮ፣ በሙዚቃና በዳንስ ጩኸት ይሆናል፡፡ የማገናዘብ ችሎታ ያላቸው ፍጡራን ስሜቶች ከመመሰቃቀላቸው የተነሳ ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለማድረግ የማይታመኑ ይሆናሉ፡፡ ይህ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስሜትን መንካት ተብሎ ይጠራል፡፡ {2SM 36.2}Amh2SM 36.2

    መንፈስ ቅዱስ በእነዚህ መንገዶች፣ ግርግር ባለበት ውካታና ጫጫታ ራሱን አይገልጽም፡፡ ይህ ሰይጣን የወቅቱን ንጹህ፣ ቅን፣ ከፍ የሚያደርግ፣ የሚያከብርና የሚቀድስ እውነትን ውጤት የለሽ ለማድረግ ሲል የራሱን ተንኮል ያለባቸውን ዘዴዎች ለመሸፈን የፈለሰፈው ነገር ነው፡፡ ባለፈው የጥር ወር የሆነውን ነገር እንዳይ እንደተደረግኩ ያለ ነገር ወደ ስብሰባዎቻችን እንዲመጣ የሚያደርግ ዓይነት ሥራን ለመስራት የሙዚቃ መሣሪያዎችን ከመጠቀም ይልቅ ከሙዚቃ ጋር የተቀላቀለ አምልኮ በፍጹም ባይኖር ይመረጣል፡፡ የወቅቱ እውነት ነፍሳትን በመለወጥ ሥራው ውስጥ ምንም ዓይነት የዚህ ዓይነት ነገር አይፈልግም፡፡ ግርግር ያለበት ውካታና ጫጫታ ስሜቶችን በመረበሽ በትክክለኛ መንገድ ቢፈጸም ኖሮ በረከት የሚሆነውን ነገር በረከት እንዳይሆን ይከለክላል፡፡ የሰይጣናዊ ወኪሎች ኃይሎች የደስታ ክብረ በዓል ለማድረግ ከጋጋታና ጫጫታ ጋር ይቀላቀላሉ፣ ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ተብሎ ስም ይሰጠዋል፡፡ {2SM 36.3}Amh2SM 36.3

    ስብሰባው ሲያበቃ፣ መደረግ የነበረበት ተደርጎና ቅዱስ እውነት ቀርቦ ቢሆን ኖሮ ይደረግ የነበረው መልካም ነገር አልተፈጸመም፡፡ መነቃቃት ተብሎ በተደረገው ስብሰባ እየተሳተፉ ያሉት ወደ ስህተት የሚመራ ግንዘቤ ተቀብለው ይሄዳሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆዎችን በተመለከተ ከዚህ በፊት የሚያውቁትን ነገር መንገር አይችሉም፡፡ {2SM 37.1}Amh2SM 37.1

    የዚህ ዓይነት አምልኮ መደፋፈር የለበትም፡፡ 1844 ዓ.ም ካለፈ በኋላ ተመሳሳይ የሆነ ተጽዕኖ መጥቶ ነበር፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ እይታዎች ተደርገው ነበር፡፡ ሰዎች ስሜታቸው ተቀስቅሶ ነበር፣ ይህ የሆነው የእግዚአብሔር ኃይል እንደሆነ በታሰበ ኃይል ነበር፡፡… {2SM 37.2}Amh2SM 37.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents