Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    መጽሐፍ ቅዱስ በተአምራቶች አልተተካም

    ልዩ ስጦታዎች ወይም ተአምራዊ መገለጦች ሰዎች ለሚሰሩአቸው ሥራቸው ወይም ለያዙአቸው ሀሳቦች ትክክለኝነት ማረጋገጫ ናቸው ለሚለው ሀሳብ ማንም ሰው ዋጋ አይስጥ፡፡ እነዚህን ነገሮች በሕዝብ ፊት ካሰቀመጥን ክፉ ውጤትንና ጤናማ ያልሆነ ስሜትን ይፈጥራሉ፡፡ በሰብአዊ ልብ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ትክክለኛ ሥራ በቃሉ አማካይነት ብቃትን እንደሚሰጥ ቃል ተገብቷል፡፡ ቃሉ መንፈስና ሕይወት እንደሆነ ክርስቶስ ተናግሯል፡፡ «ውኆች ባሕርን እንደሚከድኑ ምድር የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለች” (ዕንባቆም 2፡ 14)፡፡ {2SM 100.1}Amh2SM 100.1

    ሰይጣን ሰብአዊ ፈጠራዎችን የመላእክትን ልብሶች አልብሶ ለማስተዋወቅ እጅግ ብልጠት ባለበት ሁኔታ ይሰራል፡፡ ነገር ግን ከቃሉ የሚወጣው ብርሃን በሞራል ጨለማ ውስጥ እያበራ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ በፍጹም በተአምራዊ መገለጦች አይተካም፡፡ እውነት መጠናት አለበት፣ እንደተደበቀ ሀብት መፈለግ አለበት፡፡ አስደናቂ የሆኑ ብርሃኖች ከቃሉ ውጭ ወይም የቃሉን ቦታ እንዲወስዱ አይሰጡም፡፡ በቃሉ ተጣበቁ፣ ሰዎችን ለደህንነት ጠቢባን የሚያደርገውን በውስጥ የተተከለውን ቃል ተቀበሉ፡፡ [SEE FULLER CONTEXT ON PAGES 48, 49.] {2SM 100.2}Amh2SM 100.2