Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መቅድም

    ድሮ ኢየሩሳሌም ልትሰራ በነበረችበት ወቅት ነቢዩ በራዕይ አንድ የእግዚአብሔር መልአክ ለሌላኛው መልአክ «ፈጥነህ ለዚህ ወጣት ተናገር» ሲል ሰማው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘመን ያሉ የክርስቶስ ዳግም ምጻት እንቅስቃሴ አካል የሆኑ ወጣት ወንዶችና ሴቶች የምድራችንን ታሪክ ወደ ፍጻሜ በሚያመጣው የመደምደሚያ ድራማ ውስጥ ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ ድርሻ ተሰጥቶአቸዋል፡፡MYPAmh 7.1

    «ጌታ ወጣቶችን የእርሱ አጋዥ እጆች እንዲሆኑ ሹሞኣቸዋል፡፡»Testimonies for the Church, vol. 7, p.64.MYPAmh 7.2

    «እንደ ወጣቶቻችን ካለ በደንብ የሰለጠነና የታጠቀ ሠራዊት ጋር ብንሰራ ኖሮ የተሰቀለው፣ የተነሣውና በቅርብ የሚመጣው አዳኝ መልእክት ምንኛ በፍጥነት ወደ ዓለም ሁሉ በተዳረሰ ነበር!» Education, p. 271.MYPAmh 7.3

    ከሥራችን ጅምር ጀምሮ በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ለነበሩ ወጣቶች በትንቢት መንፈስ አማካይነት የዚህ ዓይነት መልዕክቶች ይመጡ ነበር፡፡ የዚህ ስጦታ መገለጫ ለመሆን በጌታ የተመረጠችው ሚስስ ኤለን ጂ ኋይት ሥራዋን ስትጀምር የአሥራ አምስት ዓመት ልጃገረድ ነበረች፡፡ በልጅነትና በወጣትነት ዕድሜ ከጨለማ ኃይላት ጋር የሚደረገውን ትግልና በክርስቶስ በመሆን የሚገኛውን ድል አውቃለች፡፡ በቀጥታ ለወጣቶች የተፃፉ ለትምህርት የሚሆኑ ብዙ መልዕክቶች፣ የርህራሄ ቃላቶች፣ ተግሳፆችና የማደፋፈሪያ መልዕክቶች ከብዕርዋ ፈልቀዋል፡፡ እነዚህ መልዕክቶች የወጣቶችን አዕምሮ ወደ ክርስቶስና የከበረ ክርስቲያናዊ ሙሉ ወንድነትንና ሴትነትን ለመገንባት ብቸኛ ምንጭ ወደሆነው ቃሉ ሁልጊዜ በመምራት የብዙ ወጣቶቻችን ባሕርይ የሆነውን ራስን ቀድሶ የመስጠት መንፈስ ለማጠናከር ብዙ አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡MYPAmh 8.1

    ወጣቶቻችን ለክርስቲያናዊ ሥራ በቡድንና በማህበር መደራጀት እንዳለባቸው የሚገልጽ መልዕክት የተሰጠው በ1892 ዓ.ም እና በ1893 ዓ.ም ነበር፡፡ በዓለም ዙሪያ ባሉ የአድቬንቲስት ወጣቶች ሕይወት ከፍ የሚያደርግና የሚያፀና ኃይል መሆኑን ያረጋገጠ የወጣት ፈቃደኛ ሚስዮናውያን ማህበር የተመሠረተው እነዚህን ሐሳቦች መነሻ በማድረግ ነበር፡፡MYPAmh 8.2

    እህት ኋይት ለወጣቶቻችን የጻፈቻቸው ብዙ ነገሮች በመጽሐፍቶችዋ ውስጥ የሰፈሩ ቢሆኑም «ዩዝስ እንስትራክተር» በተባለውና በሌሎችም ቦታዎች የተጻፉ ብዙ ጽሁፎች በቋሚ መልክ አልተቀመጡም፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ውድ ቅርሶች ስለሆኑ በዘመኑ ወጣቶቻችን እጅ መግባት አለባቸው፡፡ በመሆኑም የጄነራል ኮንፍረንስ ፈቃደኛ ሚስዮናውያን ክፍል እርሷ ከሥራዋ ጅምር ጀምሮ የፃፈቻቸውን መጽሔቶች በሙሉ በመመርመር ለወጣቶች የሚሆነውንና የእነርሱን ችግሮች የሚመለከተውን መርጠዋል፡፡ ሙሉ ጽሁፉን ጠብቆ ማቆየት ሁልጊዜ የማይቻል ቢሆንም የወጣቶችን ጉዳይ በተመለከተ የደራሲዋን ሐሳብ በግልጽ የሚያስቀምጡ ነገሮችን በመምረጥ ረገድ ጥንቃቄ ተደርጓል፡፡ ሚዛኑን የጠበቀ የማስተማሪያ መጽሐፍ መሆን እንዲችል በመጽሐፍ መልክ ተቀምጠው ግን ለወጣቶች በብዛት ያልተሰራጩ ክፍሎችን ጨምረናል፡፡MYPAmh 8.3

    በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉትን ጽሁፎች የማሰባሰቡንና ቅደም ተከተል የማስያዙን ሥራ በህብረት የሰሩት የኤለን ጂ ኋይት ጽሁፎች አሳታሚዎችና የፈቃደኛ ሚስዮናውያን ዘርፍ ፀሐፊዎች ናቸው፡፡ የደቡብ ማተሚያ ማህበር ባደረገው ያልተቆጠበ ጥረት ይህ በምክር የተሞላ መጽሐፍ ማራኪ በሆነ መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡ ወጣቶቻችን በዚህ መጽሐፍ ላይ የሚኖራቸው ፍላጎት በትንቢት መንፈስ አማካይነት ለቅሬታዋ ቤተክርስቲያን የተላኩትን መልዕክቶች በሙሉ በጥንቃቄ ወደ ማጥናት ይመራቸዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡MYPAmh 8.4

    እነዚህ መልዕክቶች ለወጣቶቻችን ክርስቲያናዊ ባሕርይን በማነጽና በዚህ ዘመን የክርስቶስ የዳግም ምፃትን መልዕክት ለዓለም በሞላ የማድረስን ታላቅ ሥራ ወደ ፍፃሜ ለማድረስ አዲስ ኃይል እንዲሰጡና በዓለም ዙሪያ የዳግም ምጻት እንቅስቃሴ አካል ለሆኑ ወጣቶች ታላቅ ጥንካሬ እንዲሆኑላቸው ልባዊ ፀሎታችን ነው፡፡MYPAmh 8.5

    ኤም ኢ ኮርን
    በጄኔራል ኮንፍራንስ የፈቃደኛ ሚስዮናውያን ክፍል ኃላፊ
    MYPAmh 8.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents