Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መዳረሻችሁን መምረጥ

    እያንዳንዱ ሰው የራሱን መዳረሻ ወሳኝ መሆኑን ምነው ማወቅ በቻለ! በዚህ ህይወትም ሆነ በወደፊቱ ዘላለማዊ ህይወት የሚኖራችሁ ደስታ የሚወሰነው በእናንተው ነው:: ምርጫችሁ ከሆነ አሰተሳሰባችሁን፣ ቃላችሁንና ግብረገባችሁን የሚያረክሱ ጓደኞች ሊኖሩአችሁ ይችላል:: የምግብ ፍላጎታችሁንና የፍትወት ልጓማችሁን ልታላሉ ፣ ሥልጣንን ልትንቁ ፣ ሸካራ ቃላት ልትጠቀሙና ራሳችሁን እጅግ ዝቅ ወዳለው ደረጃ ልታወርዱ ትችላላችሁ:: ተጽዕኖአችሁ ሌሎችን የሚበክል ይሆንና ወደክርስቶስ ለምጣት ትችሉ ለነበራችሁት ነፍሳት መጥፊያ ምክንያት ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ከክርስቶስ፣ ትክክለኛ ከሆነ ነገር፣ ከቅድስናና ከሰማይ ልታርቁአችው ትችላላችሁ:: በፍርድ ቀን የጠፉት ወደ እናንተ እያመለከቱ «በእርሱ ተጽእኖ ባይሆን ኖር ተሰናክዬ ኃይማኖትን ማፌዣ አላደርግም ነበር:: እርሱ ብርሃን ነበረው ፣ የሰማይን መንገድ ያውቅ ነበር:: እኔ ምንም ስለ ማላውቅ ተጨፍኜ ወደጥፋት መንገድ ሄድኩ::” ይላሉ:: ኦ! ለእንደዚህ አይነቱ ክስ ምን መልስ እንሰጥ ይሆን? እያንዳንዱ ግለሰብ ነፍሳትን ወዴት እየመራ እንደሆነ ማገናዘብ በጣም አስፈላጊ ነው:: ዘላለማዊ በሆነው ዓለም እይታ ውስጥ ነን:: ተጽእኖአችን የሚያስከፍለው ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ተግተን መቁጠር አለብን፡፡ ዘላለማዊነትን ከስሌታችን ውስጥ ማስወጣት የለብንም፣ ነገር ግን ይህ የምሄድበት መንገድ እግዚአብሔርን ያስደስተዋልን? እያልን ራሳችንን ሁል ጊዜ የመጠየቅ ልምድ ሊኖረን ይገባል:: ትክክለኛ ለሆነው ነገር እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ብርሃንና መረጃ ባላቸው ሰዎች አእምሮ የእኔ ተግባር እያሳደረ ያለው ተጽእኖ ምን ይሆን?MYPAmh 28.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents