Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የድላቸው ቃልኪዳን ነው፡፡

    እግዚአብሔር ምክንያት የለሽ አይደለም የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ትላልቅና ትናንሽ ከሆኑ እቃዎች የተሰራች ነች፡፡ እግዚአብሔር ማንኛውም ምክንያት የለሽ የሆነ ነገር እንድናደርግ አይጠይቀንም፡፡ ትናንሾቹ እቃዎች የትላልቆቹን ያህል እንዲይዙ አይጠበቅባቸውም፡፡ ከእያንዳንዱ ሰው ያለውን ያህል እንዲመልስ እንጂ የሌለውን አይፈልግበትም፡፡ የተቻላችሁን አድርጉ፤ እግዚአብሔር ጥረታችሁን ይቀበላል፡፡ በአጠገባችሁ ያለውን ተግባር ተቀበሉና በታማኝነት ፈጽሙት፡፡ ያኔ ሥራችሁ ሙሉ በሙሉ በጌታ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኛል፡፡ ታላላቅ ነገሮችን ለመፈፀም ካላችሁ ፍላጎት የተነሳ እየጠበቁአችሁ ያሉትን ትናንሽ ተግባራትን ችላ አትበሉ፡፡MYPAmh 66.6

    የምስጢር ፀሎትንና የእግዚአብሔር ቃል ጥናትን ቸል እንዳትሉ ተጠንቀቁ፡፡ እነዚህ ወደ ሰማይ የምታደርጉትን ጉዞ ለማደናቀፍ የሚጥረውን የምትዋጉባቸው የጦር መሳሪያዎቻችሁ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የፀሎትና የቃል ጥናት ቸልተኝነት ሁለተኛውን ቸልተኝነት ቀላል ያደርገዋል፡፡ የመጀመሪያው ለመንፈስ ቅዱስ ተማጽኖ የሚደረግ እምቢተኝነት ለሁለተኛው እምቢተኝነት መንገድ ያዘጋጃል፡፡ በመሆኑም ልብ ይጠነክርና ህሊና ይበድናል፡፡MYPAmh 66.7

    በሌላ በኩል ደግሞ እያንዳንዱን ፈተና መቋቋም ሌላውንም ፈተና ቀላል ያደርገዋል፡፡ እያንዳንዱ ራስን መካድ ራስን መካድን ቀላል ያድርገዋል፡፡ እያንዳንዱ የተገኘ ድል ለአዳዲስ ድሎች መንገድ ያዘጋጃል፡፡ እያንዳንዱ ፈተናን መቋቋም፣ እያንዳንዱ ራስን መካድ፣ እያንዳንዱ በኃጢአት ላይ የሚገኝ ድል ለዘላለም ሕይወት የተዘራ ዘር ነው፡፡ እያንዳንዱ ከራስ ወዳድነት የፀዳ ተግባር ለመንፈሳዊነት አዲስ ጥንካሬ ይሰጣል፡፡ የበለጠውን ክቡርና እውነተኛ በመሆን የማያድግ ማንኛውም ሰው ክርስቶስን ለመምሰል መሞከር አይችልም፡፡MYPAmh 66.8

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents