Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መርሆዎች ሲነፃፀሩ

    የክርስቶስ ተከታዮች ለክርስቲያናዊ መዝናኛ በሚያደርጉት ህብረትና መብልና ደስታ ለማግኘት በሚደረግ ዓለማዊ ህብረት መካከል የጎላ ልዩነት አለ። በፀሎትና የክርስቶስንና የተቀደሱ ነገሮችን በማንሳት ፋንታ ከዓለማውያን ከንፈር የሚወጡና የሚሰሙ ነገሮች የሞኝነት ሳቅና ከንቱ ንግግሮች ናቸው። ሐሳባቸው በአጠቃላይ የሞቅታ ጊዜ እንዲኖራቸው ነው። የእነርሱ መደሰቻ በጅልነት ይጀምርና በከንቱነት ያበቃል።MYPAmh 248.3

    የእኛ ስብሰባዎች መካሄድ ያለባቸው ወደ ቤቶቻችን ስንመለስ ከእግዚአብሔር ጋርና ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ከህሊና ወቀሳ ነፃ መሆን በምንችልበት መልክ ነው። በማንኛውም መንገድ ቢሆን አብረውን የነበሩ ሰዎችን እንዳላቆሰልናቸውና እንዳላሳዘንናቸው ወይም በእነርሱ ላይ ጎጂ የሆነ ተፅዕኖ እንዳላሳደርን እርግጠኞች መሆን አለብን።MYPAmh 248.4

    ተፈጥሮአዊው አእምሮ ራስን ወደ ማስደሰት ያዘነብላል። የዚህን ዓይነት ዝንባሌ በገፍ ማምረት የሰይጣን ፖሊሲ ነው። ሰዎች «የነፍሴ ጉዳይ እንዴት ነው?” የሚለውን ጥያቄ ለማንሳት ጊዜ እስኪያጡ ድረስ አእምሮዋቸውን በዓለማዊ መደሰቻ ፍላጎት ለመሙላት ይሻል። የደስታ ፍቅር ተላላፊ (ተዛማች) ነው። ለዚህ አልፎ የተሰጠ አእምሮ ተጨማሪ ደስታን በመሻት ከአንዱ ነጥብ ወደ ሌላው ይቸኩላል። ለእግዚአብሔር ህግ መታዘዝ ይህንን ዝንባሌ ይቃወምና እግዚአብሔር ለማይወዳቸው ነገሮች መከላከያ ያበጃል። Counsels to Teacher, Parents and Students, P 336-337.MYPAmh 248.5

    ወጣቶች ለተሰጡአቸው እድሎች፣ የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀማቸውና ችሎታዎቻቸውን በትክክል ለመጠቀማቸው በእግዘአብሔር ፊት ምላሽ ይሰጣሉ። ታዲያ ምንም ዓይነት መዝናናት ወይም መደሰት አያስፈልግም ማለት ነው? ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ። ምንም ሌላ ነገር ሳናደርግ መሥራት፣ መሥራት፣ መሥራት ብቻ ነው ወይ የሚጠበቅብን?MYPAmh 248.6

    የእግዚአብሔር በረከት በላዩ እንዲያርፍ በእምነት ጠይቃችሁ የምታደርጉት ማንኛውም መደሰቻ አደገኛ አይሆንም። ነገር ግን የምስጢር ፀሎቶቻችሁን እንዳትፀልዩ፣ በፀሎት መሰዋያው ላይ ራሳችሁን እንዳታቀርቡ ወይም በፀሎት ስብሰባዎች ላይ እንዳትሳተፉ የሚያደርጉአችሁ መደሰቻዎች አደገኛ ናቸው። Counsels to Teacher, Parents and Students, P. 367.MYPAmh 248.7

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents