Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ

    ጌታ ኢየሱስ ሥራውን የሚሰራው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ተወካይ ነው፡፡ በርሱ አማካይነት መንፈሳዊ ሕይወትን በነፍስ ውስጥ በመላክ የግለሰቡን ኃይሎች ለመልካም ያነሳሳል፡፡ ከግብረገብ እርኩሰት በማጥራት ለመንግስቱ ገጣሚ ያደርገዋል፡፡ ኢየሱስ ለሰዎች ሊሰጥ ያለው ብዙ በረከቶችና ሊያከፋፍል ያለው የበለፀጉ ሥጦታዎች አሉት:: እርሱ ድንቅ፣ መካርና በጥበብና በብርታት ወሰን የለሽ ነው፡፡ የመንፈሱን ኃይል አምነን ከተቀበልንና በእርሱ ለመቀረጽ ፈቃደኛ ከሆንን በርሱ ሙሉ ሆነን እንቆማለን፡፡ እንዴት ያለ ግሩም ሐሳብ ነው! በክርስቶስ «የመለኮት ሙላት በአካል ያድራል፤ እናንተም በእርሱ ምሉዓን ናችሁ” ይላል፡፡ የሰው ልብ በእግዚአብሔር መንፈስ ለመቀረጽ ፈቃደኛ እስኪሆን ድረስ ደስታ ሊያገኝ አይችልም፡፡ መንፈስ ቅዱስ የታደሰውን ነፍስ ምሳሌ ከሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንዲስማማ ያደርጋል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ አማካይነት ለእግዚአብሔር ያለው ጠላትነት ወደ እምነትና ፍቅር ይለወጣል፤ ትዕቢትም ወደ ትህትና ይለወጣል፡፡ ነፍስ የእውነትን ውበት ትመለከትና በባሕርይ ውበትና ፍጽምና ክርስቶስ ይከበራል፡፡ እነዚህ ለውጦች ሲፈጸሙ የሰማይ መላእክት አስደናቂ ዝማሬ ይዘምራሉ፤ አምላክና ክርስቶስ በመለኮታዊ አምሳል በተለወጡ ነፍሳት እጅግ ደስ ይላቸዋል፡፡MYPAmh 42.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents