Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የብቃት መስፈርቶች

    በወጣቶች ላይ ከባድ ሃላፊነት አለ፡፡ ብርሃንና እውቀት በጨመረበት በዚህ ትውልድ ከሚኖሩ ወጣቶች እግዚአብሔር ብዙ ይጠብቅባቸዋል፡፡ ይህንን ብርሃንና እውቀት ለሌሎች እንዲያጋሩ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የብዙዎችን አእምሮ እያጨለመ ያለውን ስህተትና ጥንቆላ እንዲያስወግዱ ይሻል፡፡ እያንዳንዱን የእውቀትና የልምድ ጠብታና ዘርፍ በማሰባሰብ ራሳቸውን ማሰልጠን አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር ለሰጣቸው ለያንዳንዱ እድሎችና ምቹ አጋጣሚዎች ተጠያቂ ያደርጋቸዋል፡፡ ከፊታቸው ያለውን ሥራ እንደ ጊዜው አስፈላጊነት ወደ ፊት ከቦታ ወደ ቦታ ለመውሰድ የእነርሱን ልባዊ የሆነ ጥረት ይጠብቅባቸዋል፡፡MYPAmh 34.1

    ወጣቶች አእምሮአቸውንና ልባቸውን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ቢቀድሱ ኖሮ ከፍ ወዳለው የብቃትና ጠቃሚነት ደረጃ በደረሱ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ወጣቶች እንዲደርሱበት የሚፈልገው የብቃት ደረጃ ይህ ነው፡፡ ከዚህ በታች ፈጽሞ መገኘት እግዚአብሔር የሰጣቸውን ምቹ አጋጣሚዎች በአግባቡ ለመጠቀም እምቢተኛ መሆን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጠላት ጋር እንደ መወገንና ለሰብዓዊ ዘር በጎነት ለመስራት እንደ አለመፈለግ ይታያል፡፡MYPAmh 34.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents