Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ፅኑ መሠረት ያለው ተስፋ

    በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘታችሁን እንዴት ታውቃላችሁ? ቃሉን በፀሎት አጥኑ። ሌሎችን መጽሐፍት ለማንበብ ስትሉ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን ወደ ጎን አታስቀምጡት። መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአተኛነታችንን እንድናምን ያደርገናል። የደህንነትን መንገድ በግልፅ ያስቀምጥልናል። ብሩህና የከበረ ሽልማትን ወደ እይታችን ያመጣልናል። የተሟላ ደህንነትን ይገልጥልናል! ይህንን ደህንነት ማግኘት የሚቻለው በእርሱ ወሰን የለሽ ምህረት ብቻ መሆኑንም ያስተምራል።MYPAmh 176.1

    የሚስጢር ፀሎት የሐይማኖት ነፍስ ስለሆነ ችላ አትበሉት። ለነፍስ ንፅህና ልባዊና የጋለ ጸሎት በማድረግ ለምኑ። ይህ ሟች ሕይወታችሁ በአደጋ ላይ በሚሆንበት ጊዜ እንደምታደርጉት ከልባችሁ ሁናችሁ በናፍቆት ፀልዩ። በውስጣችሁ ለደህንነት ያለው ሊገለፅ የማይቻል ናፍቆት እስኪሟላና ለኃጢአታችሁ ይቅርታ ስለ ማግኘታችሁ ጣፋጭ ማረጋገጫ እስኪገኝ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ቆዩ።MYPAmh 176.2

    የዘላለም ሕይወት ተስፋን አቅልላችሁ መቀበል የለባችሁም። በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ለዘላለም መፈፀም ያለበት ጉዳይ ነው። ባዶ ተስፋ ጥፋታችሁን ያረጋግጣል። የምትቆሙትም ሆነ የምትወድቁት በእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ስለ ራሳችሁም ምስክርነት መሻት ያለባችሁ በዚያው ቃል ውስጥ ነው። እዚያ ክርስቲያን ለመሆን ከእናንተ ምን እንደሚጠበቅ ማየት ትችላላችሁ:: ድል እስክታገኙና በአዳኛችሁ አሸናፊዎች እስክትሆኑ ድረስ የጦር መሣሪያችሁን አታስቀምጡ፣ ወይም ከጦር ሜዳ አትውጡ። Testimonies for the Church, vol. 1, P163 -164.MYPAmh 176.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents