Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የእውነተኛ ሃይማኖት ተግባራዊነት

    አንዳንዶች ከፍ ያለ የእምነት ቀናኢነት እውነተኛ አገልግሎትን ያካክሳል በማለት ታላቅ ስህተት ይሰራሉ፡፡ ነገር ግን ተግባራዊ ያልሆነ ኃይማኖት እውነተኛ አይደለም፡፡ እውነተኛ መለወጥ ከመሰሎቻችን ጋር በሚኖረን ግንኙነት በጥብቅ ታማኝ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ በየእለቱ ሥራችን ታማኞች እንድንሆን ያደርገናል፡፡ እያንዳንዱ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይማኖት መክሊቶቹን ለጌታ አገልግሎት እንዲጠቀም ብቁ እንደሚያደርገው ያሳያል፡፡ MYPAmh 53.6

    «በስራው ሰነፍ አይደለም፡፡” እነዚህ ቃላት በያንዳንዱ ክርስቲያን ሕይወት ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡ ምንም እንኳን ሥራህ የማይስብ ቢመስልም አንተ የምታከናውንበት ዘዴ የከበረ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሥራህን ለጌታ እንደምትሰራ አድርገህ ሥራ:: ሥራህን በደስታና በአክብሮት ሥራ፡፡ በጌታ ዘንድ ሥራችን ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉት በሥራችን ውስጥ የሚመጡ የከበሩ መርሆዎች ናቸው:: እውነተኛ አገልግሎት በምድር ላይ ያሉትን ዝቅተኞቹን አገልጋዮች ከፍ ብለው በሰማይ አደባባይ ካሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ጋር ያቆራኛል፡፡ MYPAmh 53.7

    እንደ እግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ክርስቲያኖች በወንጌል ውስጥ ወደ ተቀመጠላቸው ከፍ ያለ ደረጃ ለመድረስ መጣር አለባቸው፡፡ ከፍጽምና ባነሰ ነገር የሚረኩ መሆን የለባቸውም፡፡ ክርስቶስ «የሰማዩ አባታችሁ ፍፁም እንደሆነ እናንተም ፍፁማን ሁኑ» ብሏል፡፡MYPAmh 54.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents