Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የምክር ቃላት

    የአእምሮና የአካል ኃይሎችን ማሰልጠን በእግዚአብሔር ስርአት ውስጥ ነው! ነገር ግን የአካል እንቅስቃሴው ባሕርይ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ከሰጣቸው ትምህርቶች ጋር ሙሉ በሙሉ የሚስማማ መሆን አለበት። በተማሪዎችና በመምህራን ትምህርትና ራስን በማሰልጠን ስራ ላይ የሰማይ ወኪሎች ስለ እነርሱ “ዓለምን የሚወዱ” የሚል ጽሁፍ በመዝገባቸው ላይ እንዳይጽፉባቸው እነዚያ ትምህርቶች በክርስቲያኖች ሕይወት መታየት አለባቸው። ለብዙዎች “ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ” የሚል ጽሁፍ አሁን እየተፃፈባቸው ነው። 2ጢሞ 3፡4MYPAmh 240.1

    በመሆኑም ሰይጣንና መላእክቱ ለነፍሳት ወጥመዳቸውን እያጠመዱ ናቸው። የመምህራንና ተማሪዎች አእምሮ ሙሉ በሙሉ በሚመስጡ የአካል እንቅስቃሴዎችና መደሰቻዎች እንዲያዙ ለማድረግ እየሰሩ ናቸው። ይህም ዝቅተኛ ስሜቶችን የማጠናከር ባሕርይ ያላቸውንና የእግዚአብሔር መንፈስ በሰዎች ልቦች የሚሰራውን ስራ የሚቃወሙ የምግብ ፍላጎቶችንና ስሜቶችን የሚፈጥር ነው።MYPAmh 240.2

    በትምህርት ቤት ያሉ መምህራን በሙሉ እንቅስቃሴና የስራ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል። ይህ ደግሞ ምን መሆን እንዳለበት እግዚአብሔር አመልክቷል! ያውም ጠቃሚ የሆነ የተግባር ስራ ነው። ነገር ግን ብዙዎች የሰው ግኝቶችን ለመከተልና መንፈሳዊ ሕይወትን ለማደናቀፍ ከእግዚአብሔር ርቀዋል። መደሰቻዎች የመንፈስ ቅዱስ ስራን ለመቃወም ከማንኛውም ነገር ይልቅ የበለጠ እየሰሩ ናቸው! በዚህም ጌታ አዝኗል…።MYPAmh 240.3

    “ራሳችሁን የምትገዙና የነቃችሁ ሁኑ! ምክንያቱም ጠላታችሁ ሰይጣን የሚውጠውን ሰው ፈልጎ በዙሪያችሁ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና።” 1ጴጥ 5፡8። •እርሱ ራሳችሁን የምታስደስቱባቸውን ሁኔታዎች በመመልከት በጨዋታ ሜዳ ውስጥ ነው። ከአደጋ ያልተጠበቀውን እያንዳንዱን ነፍስ በመያዝ፣ በሰው ልብ ውስጥ ዘሩን በመዝራትና የሰውን አእምሮዎች በመቆጣጠር በጨዋታ ሜዳ ውስጥ ነው። በትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ በሚደረግ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውስጥ እርሱ አለ።MYPAmh 240.4

    አእምሮዎቻቸው በጨዋታዎች እጅግ ጠልቀው እንዲያዙ የሚያደርጉ ተማሪዎች ለእነርሱ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ትምህርት፣ ምክርና ተግሳጽ ለመቀበል በተሻለ ሁኔታ ውስጥ አይደሉም፡፡ የአካል እንቅስቃሴ የተፈቀደው በጥበብ አምላክ ነው፡፡ ተማሪዎች ለእነርሱ እጅግ አስፈላጊ የሆኑትን ተግባራዊ ሥራዎች እንዲማሩ በየቀኑ የተወሰኑ ሰዓታት መስጠት አለባቸው፡፡MYPAmh 240.5

    በእያንዳንዱ ትምህርት ቤትም ሆነ ተቋም ያለ እያንዳንዱ ግለሰብ ልክ እንደ ዳንኤል በሁሉም አቅጣጫ እጅግ ከፍ ወዳለው ደረጃ ለመድረስ ከሚያስችል የጭበብ ምንጭ ጋር ግንኙነት የመፍጠር አስፈላጊነት አለ፡፡ በዳንኤል ፊት እግዚአብሔርን መፍራትና መውደድ ነበር፡፡ ለእግዚአብሔር ተገዥ መሆኑን በመገንዘብ በተቻለው መጠን ለታላቁ መምህር የፍቅር ጥንቃቄ ምላሽ ለመስጠት ያሉትን ኃይሎች በሙሉ አሰለጠናቸው፡፡ አራቱ የዕብራውያን ወጣቶች የራስ ወዳድነት አስተሳሰብና የደስታ ፍቅር የሕይወትን ወርቃማ ጊዜያቶች እንዲይዙ አልፈቀዱም፡፡ ፈቃደኛ በሆነ ልብና በተዘጋጀ አእምሮ ሰሩ፡፡ ይህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ወጣት መድረስ ከሚችለው ደረጃ በላይ የሆነ ነገር አይደለም፡፡ Counsels to Teachers, Parents & Students, P. 281-284.MYPAmh 240.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents