Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክርስቲያናዊ መዝናኛ

    የአካልና የአእምሮ ኃይላቸውን ለእግዚአብሔር ክብር ከመጠቀም ዓላማ በመነሳት ክፋት በሌለበት መዝናናት መንፈሳቸውን ማደስና አካሎቻቸውን ማነቃቃት ለክርስቲያኖች እድልና ተግባራቸው ነው። የእኛ መዝናኛዎች የከንቱነትን መልክ የያዙ ትርጉም የለሽ መደሰቻዎች መሆን የለባቸውም። የመዝናኛ ፕሮግራሞቻችንን ከእኛ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች ከፍ ሊያደረጉና ሊጠቅሙ በሚችሉበት መልክና እኛንና እነርሱንም በአጠገባችን ያሉትን ተግባራት እንደ ክርስቲያኖች በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም እንድንችል ብቁ በሚያደርገን መልኩ ማዘጋጀት እንችላለን።MYPAmh 236.4

    ተራ የሆኑ የሕይወት ተግባራትን በታማኝነት መፈፀም እንዳንችል ሊያደርጉ በሚችሉ መደሰቻዎች ላይ የምንሳተፍ ከሆነና ይህንን በማድረጋችንም ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሰማያዊ ነገሮች ለማሰላሰል ያለንን ፍቅር የምንቀንስ ከሆነ በእግዚአብሔር ዓይን ይቅር አንባልም። የክርስቶስ ሃይማኖት ተፅእኖ ደስታን የሚያመጣና ከፍ የሚያደርግ ነው። እንደ የሞኝነት ቀልድና ፌዝ፣ ከንቱነት፣ የሞኝ ወሬ ከመሳሰሉ ነገሮች ሁሉ በላይ ነው። በመዝናኛ ጊዜያችን በሙሉ እጅግ በተሳካ ሁኔታ ሕይወታችንን ወደ ንፅህና፣ እውነተኛ መልካምነትና ቅድስና ከፍ ለማድረግ ከመለኮታዊ የብርታት ምንጭ አዲስ ብርታትና ድፍረት እንሰበስባለን።MYPAmh 236.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents