Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክርስቲያናዊ መዝናኛ

    መንፈሳችንን ለማደስና አካሎቻችን ብርታት እንዲያገኙ ስንሻ ሳለ ሁልጊዜ እግዚአብሔር ያሉንን ኃይሎች ከሁለም ለተሻለ ዓላማ እንድንጠቀም ይፈልግብናል። መዝናኛዎቻችንን በላያችን የተጣሉብንን ኃላፊነቶች በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት በተሻለ ሁኔታ ገጣሚዎች እንድንሆን በሚያደርግ መልኩና ተፅዕኖአችንም ከእኛ ጋር ግንኙነት ለሚፈጥሩ ሰዎች ጠቃሚ ሊሆን በሚችል መልኩ ማድረግ እንችላለን! ማድረግም አለብን። ከእንደዚህ ዓይነት ቦታዎች በአእምሮ ተሻሽለንና በአካል ታድሰን እንደዚሁም በተሻለ ተስፋና ድፍረት ሥራችንን በአዲስ መንፈስ ለመጀመር ወደ ቤታችን እንመለሳለን።MYPAmh 248.1

    እኛ በዚህች ምድር ላይ ያለነው ሰብዓዊ ዘርን ለመጥቀምና ለህብረተሰቡ በረከት ለመሆን ነው። ከንቱነትና ሞኝነት ብቻ በአእምሮአቸው ውስጥ እንዲመላለስ የሚሹ ብዙዎች እንደሚያደርጉት ሁሉ እኛም አእምሮአችን በዚያ ዝቅ ባለ መስመር ላይ እንዲሄድ ከፈቀድን ለህዝባችንና ለትውልዳችን እንዴት ጠቃሚዎች መሆን እንችላለን? በዙሪያችን ላለው ህብረተሰብ እንዴት በረከት መሆን እንችላለን?...MYPAmh 248.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents