Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መሻትን መግዛት ትልቅ ሽልማት አለው

    ዛሬ እንደ ዳንኤል የሚደፍሩና የሚፈለግባቸውን የሚያደርጉ ወጣቶች ይፈለጋሉ፡፡ ዛሬ በዓለም ውስጥ ንፁህ ልቦችና ጠንካራና የማይፈሩ እጆች ይፈለጋሉ፡፡ ሰው ያለማቋረጥ ራሱን እያሻሻለ በየቀኑ ወደ ከፍተኛ የብቃት ደረጃ እንዲደርስ ነበር እግዚአብሔር ያቀደው፡፡ ራሳችንን ለመርዳት የምንሻ ከሆንን እርሱ ይረዳናል፡፡ በሁለቱ ዓለማት ደስታን የማግኘት ተስፋችን የሚወሰነው አንዱን በአግባቡ መጠቀማችን ላይ ነው፡፡ በየቦታው ወደ መሻትን አለመግዛት የሚያመራውን አቀራረብ በጥንቃቄ ልንከላከል ይገባል፡፡MYPAmh 159.3

    ውድ ወጣቶች፣ በፀጋው ልታድጉ የምትችሉበትን ሥራ እንድትሰሩ እግዚአብሔር ይጠራችኋል፡፡ «ሰውነታችሁን ሕያው፣ ቅዱስና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መስዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤ ያውም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው፡፡» እግዚአብሔር በሰጣችሁ ወንድነታችሁና ሴትነታችሁ ቁሙ፡፡ ሕይወታችሁ ከዳንኤል ሕይወት ጋር ተነፃፃሪነት እስኪኖረው ድረስ በምግብ ፍላጎቶቻችሁ፣ ልምዶቻችሁና ለነገሮች ባላችሁ ስሜት ንጽህናን አሳዩ፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ እግዚአብሔር ሰማያዊ በሆኑ ነርቮች፣ በጠራ አእምሮ፣ ባልደበዘዘ ፍርድ አሰጣጥና ጥልቅ በሆነ ነገሮችን የመለየት ችሎታ ይባርካችኋል፡፡ የሕይወት ደንባቸው ጽኑና የማይዋዥቅ የሆኑ የዛሬ ወጣቶች በአካል፣ በአእምሮና በነፍስ ጤንነት ይባረካሉ፡፡ The Youth’s Instructor, July 9,1903.MYPAmh 159.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents