Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ልብን የሚመረምሩ ጥያቄዎች

    ኦ ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን በመረመሩና በተመሳሳይ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆን ክርስቶስ እንዲህ ያደርግ ነበርን ብለው በመጠየቅ የሚያስቡትን ነገር ቢያደርጉ ምንኛ መልካም ነበር! ከሰማይ እውቀትን ለማግኘት የተሰጡን መልካም ዕድሎች ታላቅ ሃላፊነት ውስጥ አስቀምጠውናል:: ስለዚህ ጥልቅ በሆነ የሃላፊነት ስሜት በተሰጠኝ ብርሃን እየተመላለስኩበት ነውን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን:: ከተሰጠኝ ታላቅ ብርሃን አንፃር ሰዎችን በትክክለኛ መንገድ ላይ እየመራሁ ነኝ ወይስ ሽባዎች ሊሄዱበት የማይችሉትን ጠማማ መንገድ እየሰራሁ ነኝ? …..MYPAmh 28.2

    ሁለመናችን ጥልቅ በሆነ፣ በውስጣችን በሚኖር እሳት፣ ቅድስናና በእውነት ሥልጣን መወረር አለበት:: ውድ ወጣት ሆይ፣ የሰማይ ብርሃን ብሩህ ጨረሮች በመንገድህ ላይ እያበሩ ስለሆነ ያሉህን መልካም ዕድሎች በደንብ እንድትጠቀምባቸው እፀልያለሁ:: ሰማይ የላከውን እያንዳንዱን የብርሃን ጨረር ተቀበልና ተጠንቀቅለት:: ያኔ መንገድህ እስከ ሙሉ ቀን ብርሃን ድረስ እየበራ ይሄዳል::—The Youth’s Instructor, February 2, 1893.MYPAmh 28.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents