Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እንክርዳድ መዝራት

    ውድ ወጣት ወዳጆች ሆይ፣ እንክርዳድን በመዝራት ያሳለፋችሁት ጥቂት ጊዜ ሕይወታችሁን በሙሉ መራራ የሚያደርግ እህል ያመርታል። በሐሳብ የለሽነት የፈፀማችሁት የአንድ ሰዓት ስህተት፣ አንድ ጊዜ ለፈተና መሸነፍ የህይወታችሁን እንቅስቃሴ ወደ ስህተት አቅጣጫ ሊያመራው ይችላል። የምታሳልፉት የወጣትነት ጊዜ አንድ ብቻ ስለሆነ ያንን ጊዜ ጠቃሚ አድርጉት። አንዴ ካለፋችሁበት በኋላ ስህተቶቻችሁን ለማስተካከል በፍፁም መመለስ አትችልም። ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት እምቢ የሚልና ራሱን በፈተና መንገድ ላይ የሚያስቀምጥ ሰው በርግጥ ይወድቃል።MYPAmh 272.1

    እግዚአብሔር እያንዳንዱን ወጣት እየፈተነ ነው። ብዙዎች ለግድ የለሽነታቸውና አክብሮት የለሽ ለመሆናቸው ምክንያት የሚሰጡት ከእነርሱ የበለጠ ልምድ ያላቸው መምህሮቻቸው ባሳዩአቸው መጥፎ ምሳሌ መሆኑን ነው። ነገር ግን ይህ ማንንም ሰው ትክክል የሆነ ነገር ከማድረግ ማገድ የለበትም። በመጨረሻው የፍርድ ቀን አሁን እንደምታቀርቡት ዓይነት ምክንያት ማቅረብ አትችሉም። መንገዱን አውቃችሁ ልትሄዱበት ባለመምረጣችሁ ፍትሃዊ ፍርድ ይሰጣችኋል።MYPAmh 272.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents