Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሚሠራ ሥራ

    ወጣት ወንዶችና ሴቶች እግዚአብሔር እናንተ የምትሠሩት ሥራ እንዳለው አየሁ፡፡ መስቀላችሁን ተሸከሙና ክርስቶስን ተከተሉት፡፡ ካልሆነ ለእርሱ የማትገቡ ናችሁ፡፡ ምንም ጥራት በሌለበት ግድየለሽነት ውስጥ ሆናችሁ ስለ እናንተ የእግዚአብሔር እቅድ ምን እንደሆነ እንዴት መናገር ትችላላችሁ? እንደ ታማኝ አገልጋዮች የጌታን ፍቃድ ካልፈፀማችሁ በቀር እንዴት መዳንን ትጠብቃላችሁ? የዘላለም ሕይወት የሚያገኙ በሙሉ ሥራቸውን በትክክል የሚፈጽሙ ናቸው፡፡ የክብር ንጉሥ ለእነርሱ፡- «አንተ መልካምና ታማኝ ባሪያ ተግባርህን ተወጥተሃል፡፡» እያለ በቀኝ እጁ በኩል ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል፡፡ በጌታህ የአታክልት ቦታ ምን አይነት ሥራ መሥራት እንደምትችል ከመሻት ይልቅ ስለ ስራህ ደስታ ማግኛ ዘዴዎች ጥናት እያደረግክ ሳለ ምን ያህል ነፍሳት ከጥፋት ማዳን እንደምትችል እንዴት መንገር ትችላለህ? እነዚህን ስብሰባዎች ለውይይት ያደረጉና የሙዚቃ ልምምዱንም ለነፍሳት መዳን ምክንያት ያደርጉ ስንቶች ናቸው? እስካሁን ወደ ዳነ አንድ ነፍስ ማመልከት ካልቻልክ ተመለስ፡፡ ኦ ወደ አዲስ የተግባር አቅጣጫ ተመለስ፡፡ ለነፍሳት መፀለይ ጀምር፡፡ ወደ ክርስቶስ አጠገብ፣ ወደሚደመው ጎኑ ቅረብ፡፡ ትሁትና ፀጥ ያለ መንፈስ ሕይወታችሁን ያስውበው፤ ልባዊ የሆነ፣ ከተሰበረ ልብ የሚመነጭና የዋህነት ያለበት ልመና የራሳችሁን ነፍስ ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ነፍስ ለማዳን የሚያስችል ጥበብን ለማግኘት ወደ እርሱ ይውጣ፡፡MYPAmh 136.1

    ከምትዘምሩት የበለጠ ፀልዩ፡፡ ከመዘመር ይልቅ መፀለይ እጅግ በሚያስፈልግበት ቦታ አትቆሙምን? ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሆይ! ጌታ እንድትሰሩ፣ ለእርሱ እንድትሰሩ እየጠራችሁ ነው፡፡ የተግባር አቅጣጫችሁን ሙሉ በሙሉ ቀይሩ፡፡ በቃልና በቤተክርስቲያን ልዩ ትምህርት የሚያገለግሉ መሥራት የማይችሉትን ሥራ ትሰራላችሁ፡፡ አገልጋይ ሊደርሳቸው ያልቻላቸውን ክፍሎች መድረስ ትችላላችሁ፡፡ Testimonies for the Church,vol. 1, P.511-513.MYPAmh 136.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents