Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጤናን መጠበቅ

    ጤና ያለውን ዋጋ ጥቂቶች ብቻ የሚያደንቁት በረከት ነው፡፡ ሆኖም የአእምሮአችንና የአካላችን ብቃት በአብዛኛው የሚደገፈው በጤንነት ላይ ነው፡፡ ትርታዎቻችንና ስሜቶቻችን መቀመጫቸው በአካል ውስጥ ስለሆነ አካላዊ ጤንነታችን በተሸለ ሁኔታና መክሊቶቻችንን እስከ መጨረሻ መጠቀም በምንችልበት በተሻለ መንፈሳዊ ተጽእኖ ሥር መጠበቅ አለባቸው፡፡ ማንኛውም የአካል ብርታትን የሚቀንስ ነገር አእምሮን ደካማ በማድረግ በትክክለኛና ትክክል ባልሆነ ነገር መካከል የመለየት አቅምን ይቀንሳል፡፡MYPAmh 153.1

    የአካል ኃይሎቻችንን ያለ አግባብ መጠቀም ሕይወታችን ለእግዚአብሔር ክብር የሚውልበትን ጊዜ ያሳጥርና እግዚአብሔር እንድንሰራለት የሰጠንን ሥራ ለመሥራት ገጣሚዎች እንዳንሆን ያደርገናል፡፡ ሌሊት እስከ ረፋድ በመቆየትና ጤናችንን እስከመሰዋት ድረስ ለምግብ ፍላጎት ራሳችንን በማስገዛት እኛነታችንን ለመጥፎ ልምዶች ተገዥ ስናደርግ የደካማነትን መሠረት እየጣልን ነን…፡፡MYPAmh 153.2

    ስለዚህ የተፈጥሮ ሕግን በመጣስ ሕይወታቸውን የሚያሳጥሩና ራሳቸውን ለአገልግሎት ገጣሚ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ ሰዎች እግዚአብሔርን በመቀማት ወንጀል ተጠያቂ ናቸው፡፡ እንዲሁም የእነርሱን መሰል ሰዎችንም እየቀሙ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር እንዲሰሩለት ወደ ዓለም የላካቸው ሌሎችን የመባረክ ዋና ሥራ በተከተሉት መጥፎ መንገድ በአጭሩ ተቀጭቷል፡፡ ባላቸው አጭር ጊዜ ውስጥ ሊፈጽሙት ለሚችሉት ሥራ እንኳን ራሳቸውን ገጣሚ አላደረጉም፡፡ ጎጂ በሆኑ ልምዶቻችን ምክንያት ዓለምን መልካም ነገር እንዳያገኝ ስንከለክል እግዚአብሔር በጥፋታችን ተጠያቂ ያደርገናል፡፡MYPAmh 153.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents