Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ራስን መመርመር

    ራስን በጥልቀት የመመርመርና በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን የመፈተሸ አስፈላጊነት አለ፡፡ በልቤ ጢናማ ነኝ ወይስ የበሰበስኩ ነኝ? በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ነኝ ወይስ ውጫዊ አዲስ ልብስ የለበስኩ፣ በልቤ ውስጥ ግን ሥጋዊ ነኝ? እራሳችሁን በእግዚአብሔር የፍርድ ዙፋን ፊት አቅርቡና በእግዚአብሔር ብርሃን የተደበቀ ኃጢአት ወይም በደል ወይም ማንኛውም መስዋዕት ያላደረጋችሁት ጣኦት ካለ እዩ፡፡ በሰይጣን ማታለያዎች እንዳትታለሉ ፀልዩ፤ አዎን ከዚህ በፊት ፀልያችሁ በማታወቁት ሁኔታ ፀልዩ ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ግንዛቤ ለጎደለው፣ ግድ የለሽ ለሆነውና ከንቱ መንፈስ አልፋችሁ እንዳትሰጡና ኃይማኖታዊ ተግባራትን የህልና ወቀሳን ፀጥ ማድረግያ እንዳታደርጉት ነው፡፡MYPAmh 60.3

    የመጨረሻው ቀናት ምልክቶች ከሆኑት ኃጢአቶች አንዱ ክርስቲያን ነን ባዮች ከእግዚአብሔር ይልቅ ደስታ ወዳዶች መሆናቸው ነው፡፡ ከነፍሳችሁ ጋር በእውነት ተነጋገሩ፡፡ በጥንቃቄ መርምሩ፡፡ ራሳቸውን በታማኝነት ከመረመሩ በኋላ ወደ ሰማይ በመመልከት «ከላይ ከተገለፁት መካከል አንዱ አይደለሁም፤ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላ ወዳጅ አይደለሁም» የሚሉት ምንኛ ጥቂት ናቸው፡፡ «ለዓለም ሞቻለሁ፤ እኔ ዛሬ የምኖረው ህይወት በእግዚአብሔር ልጅ ባለኝ እምነት ነው፡፡ ሕይወቴ ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ተሰውራለች፤ ሕይወቴ የሆነው እርሱ በሚገለጥበት ቀን እኔም ከርሱ ጋር በክብር እገለጣለሁ» ለማለት የሚችሉ ምንኛ ጥቂቶች ናቸው፡፡MYPAmh 60.4

    የእግዚአብሔር ፍቅርና ፀጋ! ኦ ውድ ፀጋ! ከንፁህ ወርቅ ይልቅ የበለጠ ዋጋ ያለው ጸጋ መንፈስን ከማንኛውም መርሆዎች የበለጠ ከፍ ያለና የተከበረ ያደርጋል፡፡ ልብንና ፍቅርን በሰማይ ያደርጋል፡፡ በዙሪያችን ያሉት በዓለማዊ ከንቱነት፣ ደስታን በመፈለግና በከንቱነት ተጣምደው እያሉ የእኛ ንግግር ግን አዳኝን በምንሻበት ጊዜ በሰማይ ይሆናል፡፡ ነፍስ ለምህረትና ለሰላም፣ ለጽድቅና ለእውነተኛ ቅድስና ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርና እላይ ያሉ ነገሮችን ማሰላሰል ነፍስን ወደ ክርስቶስ አምሳያነት ይለውጣል፡፡ Review & Herald, May 11,1886.MYPAmh 60.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents