Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ስሜትሽንና ፍላጎትሽን ማስገዛት

    አንቺ ግንዛቤ የጎደለሽ ደፋር ሁነሻል፡፡ በልብሽ ውስጥ የእግዚአብሔር ጸጋ ቦታ የለውም:: ራስሽን የጸጋው ተቀባይነትና የጽድቅ መሳሪያ አድርገሽ ማቅረብ የምትችይው በእግዚአብሔር ብርታት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር አስተሳሰብሽን ብቻ ሳይሆን ስሜቶችሽንና ፍላጎቶችሽንም እንድትቆጣጠሪ ይፈልግብሻል፡፡ ደህንነትሽ የሚደገፈው በእነዚህ ነገሮች ራስሽን መግዛት በመቻልሽ ላይ ነው፡፡ ስሜትና ፍላጎት ኃይለኛ ወኪሎች ናቸው፡፡ ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ከዋሉ፣ በተሳሳተ ዓላማ ሥር ከተደረጉ፣ ያለ ቦታቸው ከተቀመጡ ጥፋትሽን ለመፈፀም ኃይለኛ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ በአሳዛኝና ተሰፋ ቢስ ሁኔታ ውስጥ ያለ እግዚአብሔርና ያለ ተስፋ ይተውሻል፡፡MYPAmh 55.6

    ስሜቶችና ፍላጎቶች ለግንዛቤ ችሎታ፣ ለህሊና ዳኝነትና ለባሕርይ መገዛት ካለባቸው አስተሳሰብሽ ሁል ጊዜ በአዎንታዊ መልኩ ቁጥጥር ሥር መሆን አለበት፡፡ ዘላለማዊ ጥቅሞችሽን ለፍላጎትሽ መሟላት ለመሰዋት ቀርበሽ ስላለሽ በአደጋ ላይ ነሽ፡፡ ስሜት በአዎንታዊ መልኩ ሁለመናሽን በመቆጣጠር ላይ ነው፡፡ ምን ዓይነት ስሜት ነው እየተቆጣጠረሽ ያለው? እየተቆጣጠረሽ ያለው ስሜት ዝቅ ያለና አጥፊ ባሕርይ ያለው ነው፡፡ ለዚህ ስሜት ስትሸነፊ የወላጆችሽን ሕይወት መራራ ታደርጊያለሽ፤ ለእህቶችሽ ሀዘንና ሀፍረት ታመጭያለሽ፤ የራስሽን ባሕርይ መስዋዕት ታደርጊያለሽ ፤ እንደዚሁም ሰማይንና ባለ ግርማ የሆነውን ዘለዓለማዊ ሕይወት ታጭያለሽ፡፡ ይህንን ለማድረግ ዝግጁ ነሽ ወይ? ባለሽበት እንድትቆሚ እማፀንሻለሁ፡፡ በፊትሽ መከራና ሞት ስላለ በራስሽ ፈቃድ መመራትንና ዓላማ በሌለው አቅጣጫ መቀጠልሽን አቁሚ፡፡ ስሜቶችሽንና ፍላጎቶችሽን በተመለከተ ራስሽን መግዛት ካልቻልሽ በስተቀር በዙሪያሽ ባሉ ሁሉ ዘንድ ስምሽ ይጎድፍና በባሕርይሽ ላይ በሕይወት እስካለሽ ድረስ አብሮሽ የሚቆይ ሀፍረት ይሆንብሻል፡፡MYPAmh 55.7

    ለወላጆችሽ የማትታዘዢ ደፋር፣ የማታመሰግኝና ያልተቀደስሽ ነሽ፡፡ እነዚህ አሳፋሪ ባሕርያት የክፉ ዛፍ ፍሬዎች ናቸው፡፡ በግልጽ ትናገሪያለሽ፡፡ ወንዶችን ትወጂያለሽ፤ የንግግርሽ ግብም ስለ እነርሱ ቢሆን ትወጅያለሽ፡፡ «በልብ የሞላውን አፍ ይናገራል፡፡” ልምዶችሽ እስኪቆጣጠሩሽ ድረስ ጠንክረውብሻል፡፡ ዓላማሽን ለመፈፀምና ፍላጎትሽን ለማጉላት ስትይ ማታለልን ተምረሻል፡፡ Testimonies for the Church vol. 2, pp.560-562.MYPAmh 56.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents