Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እያንዳንዱን የባሕሪይ ፀጋ ማዳበር

    ለጌታ ክብር እያንዳንዱን የባሕሪይ ፀጋ ለማዳበር ጉጉ ሁን፡፡ በእያንዳንዱ የባሕሪይ ግንባታ ደረጃ እግዚአብሔርን ማስደሰት ይጠበቅብሃል፡፡ ይህንን ማድረግ ትችላለህ:: ምክንያቱም ሔኖክ በሞራል በወረደ ዘመን ውስጥ እግዚአብሔርን አስደስቶ ነበር፡፡ ዛሬ በአኛ ጊዜም ሔኖኮች አሉ፡፡ MYPAmh 68.5

    ማንኛውም ፈተና ሊያረክሰው እንዳልቻለው ታማኝ የሀገር መሪ እንደ ዳንኤል ቁም፡፡ ኃጢአትህን ለመደምሰስ የራሱን ሕይወት በመስጠት የወደደህን ጌታ አታሳዝነው፡፡ እርሱ «ያለ እኔ አንዳች ታደርጉ ዘንድ አትችሉም” ይላል፡፡ «ይህንን አስታውስ:: ስህተቶችን ፈፅመህ ከሆነና ስህተቶችህን አይተህ እንደ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ካየሃቸው በርግጠኝነት ድልን ታገኛለህ፡፡ ያኔ ጠላትን ተስፋ በማስቆረጥ አዳኙን በማስከበር ሽንፈትን ወደ ድል ትለውጣለህ፡፡ MYPAmh 68.6

    ከዚህ ዓለም ወደሚቀጥለው ይዘን የምንሄደው ብቸኛው ሐብት በእግዚአብሔር አምሳል የተመሰረተ ባሕሪይ ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ ከክርስቶስ የተማሩ ሰዎች ያገኙትን እያንዳንዱን መለኮታዊ ስኬት ከእነርሱ ጋር ወደ ሰማያዊ መኖሪያዎች ይዘው ይሄዳሉ፡፡ በሰማይ ያለማቋረጥ እየተሸሻልን እንሄዳለን፡፡ ስለዚህ በዚህ ሕይወት ባሕሪያችንን ማጎልበት ምንኛ አስፈላጊ ነው፡፡MYPAmh 68.7

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents