Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እምነትና ፀሎት

    በክርስቶስ በማመን እያንዳንዱ የባሕርይ ጉድለት ይሟላል፣ እያንዳንዱ እርኩሰት ይነፃል፣ እያንዳንዱ ስህተት ይታረማል፣ እያንዳንዱ ብቃት ይጎለብታል፡፡ MYPAmh 165.1

    “እናንተ በእርሱ ምሉአን ናችሁ”MYPAmh 165.2

    ጸሎትና እምነት የተቀራረበ ግንኙነት ያላቸው ስለሆኑ ለየብቻ መጠናት የለባቸውም፡፡ በእምነት ጸሎት ውስጥ መለኮታዊ ሳይንስ አለ፡፡ ይህ ሳይንስ እያንዳንዱ ሕይወት በስኬት ውስጥ እንዲያልፍ ሰው ማስተዋል ያለበት ሳይንስ ነው፡፡ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፡- «ማንኛውንም የምትፈልጉትን ነገር ለማግኘት ስትጸልዩ እንደሚሰጣችሁ እመኑ፣ ይሰጣችሁማል፡፡” ጥያቄያችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መሆን እንዳለበትም ግልጽ ያደርግልናል፡፡ እርሱ ሊሰጠን ቃል ለገባልን ነገሮች መፀለይ አለብን፡፡ የተቀበልነውንም ነገር የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ መጠቀም አለብን፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተስፋዎቹ ግልጽ ናቸው፡፡MYPAmh 165.3

    ለኃጢአት ይቅርታ፣ ለመንፈስ ቅዱስ፣ ክርስቶስን ለሚመስል ባሕርይ፣ ሥራውን ለመሥራት ጥበብና ብርታትን ለማግኘት፣ እርሱ ቃል ለገባልን ለማንኛውም ስጦታ መፀለይ እንችላለን፡፡ ስለዚህ እንደምንቀበል በማመን የተቀበልነውን ምስጋና ለእግዚአብሔር መልሰን መስጠት አለብን፡፡ MYPAmh 165.4

    ለበረከቱ ውጫዊ ማረጋገጫ መሻት የለብንም፡፡ ስጦታው በተስፋው ውስጥ ስላለ እግዚአብሔር ቃል የገባውን እንደሚፈጽም እርግጠኞች በመሆን ወደ ሥራችን መሄድ እንችላለን፡፡ ተሰጥቶን ያለ ሥጦታንም እጅግ በምንፈልገው ሰዓት እንገነዘበዋለን፡፡ Education, p.257-258.MYPAmh 165.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents