Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መጋረጃው ሲገለጥ

    መጋረጃው ሲገለጥ የዚህን ዘመን እርኩሰት እንዳይ ተደረግሁና ልቤ ታመመ፤ መንፈሴ በውስጤ ደከመብኝ፡፡ የምድር ኗሪዎች የኃጢአታቸውን ጽዋ እየሞሉ ነበር:: የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደ፤ ኃጢአተኞች ከምድር ላይ እስኪጠፉ ድረስ ፀጥ አይልም ነበር፡፡ MYPAmh 45.5

    ሰይጣን የክርስቶስ የግል ጠላቱ ነው፡፡ በሰማይም ሆነ በምድር የእያንዳንዱ ዓይነት የአመፅ ጀማሪ ነው፡፡ ቁጣው ይጨምራል፤ እኛ ግን ኃሉን አናስተውልም፡፡ የወደቁ መላእክት ራሳቸውን ከአደጋ ነፃ እንደሆኑ ከሚሰማቸውና ምቾት ከሚሰማቸው ጋር እንዴት እየሰሩ እንደሆነ ለማየት አይኖቻችን ቢከፈቱ ኖሮ ይህንን ያህል ደህንነት አይሰማንም ነበር፡፡ ክፉ መላእክት ሁል ጊዜ በዱካችን ናቸው፡፡ ክፉ ሰዎች ሰይጣን ሐሳብ እንደ ሰጣቸው ለመፈፀም ዝግጁ እንደሚሆኑ እንጠብቃለን፡፡ ነገር ግን አእምሮዎቻችን ከሰይጣን የማይታዩ ወኪሎች ሳይጠበቅ ሳለ አዲስ ቦታ ይይዙና በፊታችን ድንቅና ተአምራቶችን ይሰራሉ፡፡ በተሳካ ሁኔታ ልንጠቀምበት በምንችል መሣሪያ በሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለመከላከል ተዘጋጅተናል ወይ?MYPAmh 45.6

    አንዳንዶች እነዚህን ድንቆች ከእግዚአብሔር እንደሆነ ለመቀበል ይፈተናሉ፡፡ በሽተኞች በፊታችን ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡ ተአምራቶች በእይታችን ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ የሰይጣን የሐሰት ድንቆች በሙላት በሚገለጡበት ጊዜ ለሚመጣው ፈተና ተዘጋጅተናል ወይ? ብዙ ነፍሳት የሚጠመዱና የሚወሰዱ አይሆንምን? የስህተት ዓይነቶችና ከእግዚአብሔር ቃልና ከትዕዛዛቱ መለየት፣ ጆሮን ለአፈ ታሪኮች መስጠት አእምሮዎችን ለእነዚህ የሰይጣን የውሸት ድንቆች ገጣሚ እያደረጉ ነው፡፡ በቶሎ ልንገባበት ላለው ጦርነት ገጣሚዎች ለመሆን ራሳችንን ማስታጠቅ ያስፈልገናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በእምነትና በፀሎት ቢጠናና በተግባር ቢተረጎም ኖሮ ከሰይጣን ኃይል መከላከያ ጋሻ ይሆነንና በክርስቶስ ደም አሸናፊዎች እንድንሆን ያደርገናል፡፡—The Review and Herald, February 18, 1862MYPAmh 46.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents