Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ፈተና

    ታላቁ አሳች ሰይጣን ራሱን ወደ ብርሃን መልአክ በመለወጥ ወደ ወጣቶች ድብቅ ፈተናዎቹን ይዞ ይመጣና ደረጃ በደረጃ ተግባራቸውን ከሚፈጽሙበት መንገድ በማሳት ይሳካለታል። ለእርሱ ከሳሽ፣ አታላይ፣ ውሸታም፣ አሰቃይ፣ ነፍሰ ገዳይ የሚባሉ መግለጫዎች ተሰጥተውታል። “ኃጢአትን የሚሠራ ከሰይጣን ነው።” እያንዳንዱ ህግን መተላለፍ ነፍስን ለኩነኔ የሚዳርግ ከመሆኑም በላይ መለኮታዊ አለመደሰትን ይቀሰቅሳል። እግዚአብሔር የልብን ሐሳቦች ለይቶ ማየት ይችላል። ንፁህ ያልሆኑ ሐሳቦች በውስጣችን ሲኖሩ ኃጢአትን ለመፈፀምና ነፍስን ለኩነኔ ለመዳረግ በቃል ወይም በተግባር መግለጽ አያስፈልግም:: ንጽህናው ይበከልና የራስ ስሜት ያሸንፋል።MYPAmh 272.3

    እያንዳንዱ ሰው በራሱ ፍትወት ሲሳብና ሲጠለፍ ይፈተናል። የራሱን ዝንባሌዎች በመከተል ከበጎነትና ጥሩ ከሆነ መንገድ ይርቃል። ወጣቶች ለግብረገብ ታማኞች ቢሆኑ ኖሮ እጅግ ከባድ የሚባሉ ፈተናዎች በሙሉ ወደ እነርሱ የሚመጡት በከንቱ ሆነው ይቀሩ ነበር። እናንተን መፈተን የሰይጣን ሥራው ሲሆን በፈተናው መሸነፍ ግን የእናንተ ሥራ ነው። የጨለማ ኃይላት በሙሉ የሚፈተኑቱን ሰዎች ህግ እንዲተላለፉ የማድረግ ኃይል የላቸውም:: ኃጢአት ለመሥራታችን ምንም ምክንያት መስጠት አንችልም::MYPAmh 272.4

    አንዳንድ ወጣቶች ኃይሎቻቸውን በከንቱነትና በሞኝነት እያባከኑ ሳሉ ሌሎች ደግሞ እውቀትን እያጠራቀሙ፣ የህይወትን ጦርነት ለመጋጠም የጦር እቃን እየለበሱ፣ ስኬትን ለማግኘት ወስነው አእምሮአቸውን እየገሩ ናቸው። ነገር ግን የፈለገውን ያህል ከፍ ወዳለው ደረጃ ለመውጣት ቢጥሩም ፍቅራቸው እግዚአብሔርን ማዕከል ካላደረገ በስተቀር በሕይወታቸው የተሳካላቸው አይሆኑም። ትክክለኛ ነገር ለማድረግ ያላቸውን አላማ በትንሹ እንኳን ለማዳከም የሚመጡትን ሙገሣዎች እምቢ በማለት በሙሉ ልባቸው ወደ ጌታ ቢመለሱ ኖሮ በእግዚአብሔር ብርታትና መተማመን ይኖራቸዋል።MYPAmh 272.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents