Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አላማህን ከፍ አድርገህ አስቀምጥ

    እግዚአብሔር የተዋጣለትን ሥራ እንዲሰሩ የመረጣቸው ብዙዎች ትንሽ ጥረት ስለሚያደርጉ በጣም ትንሽ ሥራ ይሰራሉ፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ለኑሮአችው ምንም የተወሰነ ዓላማ እንደሌለና መድረስ የሚገባቸው የደረጃ መስፈርት እንደሌለ በማሰብ በህይወት ውስጥ ያልፋሉ፡፡ እንደዚህ አይነቶች ከስራቸው ጋር የሚመጣጠን ሽልማት ያገኛሉ፡፡MYPAmh 68.3

    እራሳችሁ ካስቀመጣችሁት ደረጃ በላይ በፍፁም መድረስ እንደማትችሉ አስታውሱ፡፡ ስለዚህ አላማችሁን ከፍ አድርጋችሁ አስቀምጡና ምንም እንኳን ወደዚያ መድረስ ከባድ ጥረትን፣ ራስን መካድንና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ቢሆንም ደረጃ በደረጃ የእድገት መሰላሉን ርቀት መውጣት አለባችሁ፡፡ ይህንን ከማድረግ ምንም ነገር እንዲያግዳችሁ አትፍቀዱ፡፡ ማንም ያለረዳትና እርግጠኛነት በሌለው ሁኔታ ውስጥ እንዲሆን እድል በዙሪያው መረቡን አጥብቆ አልጠላለፈበትም፡፡ የሚቃወሙ ሁኔታዎች እነርሱን ለማሸነፍ ጽኑ ውሳኔን መፍጠር አለባቸው፡፡ አንድ መሰናክልን መስበር ወደፊት ለመጓዝ ታላቅ ችሎታንና ድፍረትን ይሰጣል፡፡ በትክክለኛ አቅጣጫ በሙሉ ፅናት ወደፊት ግፋ፤ ያኔ ሁኔታዎች እንቅፋቶች በመሆን ፋንታ ረዳቶችህ ይሆናሉ፡፡MYPAmh 68.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents