Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ራስን መካድ

    ኢየሱስ ራሱን ባዶ ስላደረገ እርሱ ባደረጋቸው ነገሮች ሁሉ እኔነት አልታየም። ሁሉንም ነገር ለአባቱ ፈቃድ አስገዛ። በምድር ላይ የነበረው ተልዕኮው ሊያልቅ አካባቢ “በምድር ላይ አክብሬሃለሁ፤ እንድሰራው የሰጠኸኝን ሥራም ፈፅሜያለሁ” ማለት ችሏል። እኛንም ደግሞ “ከእኔ ተማሩ እኔ በልቤ ትሁትና ገር ነኝ።” “ማንም ሰው ሊከተለኝ ቢወድ ራሱን ይካድ” እያለ ይለምናል፡፡ እኔነት ከዙፋኑ ይውረድ፤ በነፍስ ላይ በፍጹም የበላይነት አይያዝ፡፡MYPAmh 107.1

    የኢየሱስን •ራስን መካድና የልብ ገርነትን የሚያይ ሰው ዳንኤል የሰው ልጅ የሚመስለውን ባየ ጊዜ “ውበቴ ሁሉ በውስጤ ወደ መበስበስ ተለወጠ” እንዳለው ለማለት ይገደዳል። ሰብዓዊ ተፈጥሮ ራሱን ለመግለፅ ሁልጊዜ ይታገላል! ለትግልም ዝግጁ ነው። ነገር ግን ከክርስቶስ የሚማር ከራስ፣ ከኩራት፣ ከሥልጣን ፍቅር የፀዳ ስለሆነ በነፍስ ውስጥ ፀጥታ አለ። ራስ ለመንፈስ ቅዱስ አሰራር ራሱን ሰጥቷል። በመሆኑም ከፍተኛውን ቦታ ለመያዝ አንጓጓም። ለመታወቅ ብለን ራሳችንን የማጨናነቅና የመጣር ፍላጎት የለንም። ነገር ግን የእኛ ከፍተኛው ቦታ በየሱስ እግር ሥር እንደሆነ ይሰማናል። እጁ እንዲመራን በመጠበቅና ድምፁ አቅጣጫ እንዲያሳየን በማድመጥ ወደ ኢየሱስ እንመለከታለን። ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህ ልምምድ ስለነበረው እንዲህ ብሏል «ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ነገር ግን እኖራለሁ። እኔ ሳልሆን ክርስቶስ በኔ ውስጥ ይኖራል። አሁን እኔ በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ራሱን ለኔ አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ባለኝ እምነት ነው።” Thoughts from the Mount of Blessing P. 30 -31.MYPAmh 107.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents