Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሕክምና ሥራ

    ፈርሃ-እግዚአብሔር ያላቸው ታማኝ ሐኪሞች ከያዙት የበለጠ አስፈላጊ የሆነ ሚስዮናዊ የሥራ መስክ የለም፡፡ አንድ ሰው ታላቅ መልካም ሥራ መሥራት የሚችልበት ወይም በዘውዱ ላይ የሚያብለጨልጩ ብዙ እንቁዎችን መማረክ የሚችልበት ከዚህ የበለጠ የሥራ መስክ የለም፡፡ እርሱ ወደሚገባበት ወደ እያንዳንዱ የሕመምተኛ ክፍል የክርስቶስን ጸጋ እንደ ጣፋጭ ሽቶ ይዞ መግባት ይችላል፡፡ በኃጢአት ለታመመችው ነፍስ እውነተኛ የሆነውን የፈውስ ዘይት ሊወስድላት ይችላል፡፡ በሽተኞችንና በሞት አፋፍ ያሉትን ሰዎች የዓለምን ኃጢአት ሁሉ ወደሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ማመልከት ይችላል፡፡ሕይወታቸው በአደጋ ላይ ላሉት ስለ ዘላለማዊ ጉዳዮች መንገር ሁኔታቸውን የከፋ ስለሚያደርግባቸው አስፈላጊ አይደለም የሚሉትን አሰተያየቶች መስማት የለባችሁም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ከአሥር ሰዎች መካከል ዘጠኙን ኃጢአትን ይቅር ባይ ስለሆነው አዳኝ ማወቅ በአካልም ሆነ በአእምሮ የተሻሉ እንዲሆኑ ስለሚያደርጋቸው ነው፡፡ ኢየሱስ የሰይጣንን ኃይል መገደብ ይችላል፡፡ በኃጢአት የታመመች ነፍስ ከአካልም ሆነ ከነፍስ በሽታ ለመፈወስ መተማመን የምትችልበት ሐኪም እርሱ ነው፡፡ Testimonies for the Church, vol. 5, p. 448-449.MYPAmh 145.7

    በሁሉም ህብረተሰብ ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ሲሰበክ የማይሰሙ ወይንም የሐይማኖት አገልግሎትን የማይከተሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በወንጌል መደረስ ካለባቸው መልእክቱ ወደ ቤታቸው መወሰድ አለበት፡፡ ብዙ ጊዜ እነርሱን መድረስ የሚቻለው በአካል ፍላጎቶቻቸው (ለጤና ችግሮቻቸው መፍትሄ በመስጠት) ነው፡፡ ለበሽተኞች የሚጠነቀቁና ለድሆች ተስፋ መቁረጥ መፍትሄ የሚሰጡ ነርሶች ከእነርሱ ጋር አብረው ለመጸለይ፣ ከእግዚአብሔር ቃል ሊያነቡላቸውና ስለ አዳኙ ለመናገር ብዙ አጋጣሚዎችን ያገኛሉ፡፡ ውስጣዊ ፍላጎታቸው ስለደከመባቸው የምግብ ፍላጎታቸውን የመቆጣጠር ብርታት ካጡት ተስፋ ቢሶች ጋር አብረው መጸለይም ሆነ ለእነርሱ ሊጸልዩላቸው ይችላሉ፡፡ ወደ ተሸነፉና ድፍረት ወዳጡ ሰዎች ሕይወት የተስፋን ጮራ ማምጣት ይችላሉ፡፡ ከሌሎች ምንም ምላሽ ሳይጠበቅ በሚደረጉ የርኅራኄ ተግባራት የሚገለጽ ራስ ወዳድነት የሌለው ፍቅር በህመም የሚሰቃዩ ሰዎች በኢየሱስ ፍቅር እንዲያምኑ ይረዳቸዋል፡፡ Ministry of Healing, P.144, 145.MYPAmh 146.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents