Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተማሪ መልካም አጋጣሚዎች

    ተማሪዎች ከመምህራኖቻችሁ ጋር ተባበሩ፡፡ ይህንን ስታደርጉ ለእነርሱ ተስፋና ድፍረት ትሰጣላችሁ፡፡ እነርሱን እየረዳችሁ ወደ ፊት ጉዞአችሁን ስትቀጥሉ ራሳችሁንም እየረዳችሁ ነው፡፡ መምህራኖቻችሁ በጽኑ ቦታ መቆማቸውና ስራቸው ስኬታማ መሆኑ በአብዛኛው የሚወሰነው በእናንተ እገዛ መሆኑን አስታውሱ፡፡ ከፍ አድርጋችሁ ስታዩ ከመምህራችሁ በስተኋላ እግዚአብሔርን እያያችሁና መምህራችሁም ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ እየሰራ እናንተ ከእርሱ የምትማሩ ትሆናላችሁ፡፡MYPAmh 120.1

    ለሥራ ያሉአችሁ መልካም አጋጣሚዎች በፍጥነት እያለፉባችሁ ናቸው፡፡ ራሳችሁን በማስደሰት የምታባክኑት ጊዜ የላችሁም፡፡ እውነተኛ ደስታ ማግኘት የምትችሉት ለስኬት ተግታችሁ ስትጥሩ ብቻ ነው፡፡ በትምህርት ቤት የምታሳልፋቸው ጊዜያቶች የተሰጡህ ወድ አጋጣሚዎች ናቸው፡፡ የተማሪነት ህይወትህን በተቻለህ መጠን ፍጹም ህይወት አድርግ፡፡ አሁን እያለፍክበት ባለው መንገድ ማለፍ የምትችለው አንዴ ብቻ ነው፡፡ ሥራህ የስኬት ወይም የውድቀት የመሆኑ ጉዳይ በአንተው እጅ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን እውቀት በማግኘት ስኬታማ ከሆንክ ለሌሎች ማካፈል የምትችለውን ሐብት እያከማቸህ ነው፡፡MYPAmh 120.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents